ኢትዮጵያውያን ወጣት ተመራማሪዎች በሩሲያ-አፍሪካ የሳይንስና ኢንጂነሪንግ ፎረም ውድድር የአንደኛ ደረጃ ዲፕሎማ አሸነፉ

© telegram sputnik_ethiopiaኢትዮጵያውያን ወጣት ተመራማሪዎች በሩሲያ-አፍሪካ የሳይንስና ኢንጂነሪንግ ፎረም ውድድር የአንደኛ ደረጃ ዲፕሎማ አሸነፉ
ኢትዮጵያውያን ወጣት ተመራማሪዎች በሩሲያ-አፍሪካ የሳይንስና ኢንጂነሪንግ ፎረም ውድድር የአንደኛ ደረጃ ዲፕሎማ አሸነፉ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 16.10.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያውያን ወጣት ተመራማሪዎች በሩሲያ-አፍሪካ የሳይንስና ኢንጂነሪንግ ፎረም ውድድር የአንደኛ ደረጃ ዲፕሎማ አሸነፉ

  

በሩሲያ ሴንት ፒተርስበርግ ከጥቅምት 2 እስከ 7 ቀን 2018 ዓ.ም ከዩኔስኮ ጋር በመተባበር በተካሄደው "የወደፊቱ የዓለም ኢንጂነሮች - የዘላቂ ልማት መሠረት" የተሰኘ የሩሲያ-አፍሪካ የወጣት ሳይንቲስቶች ፎረም ውድድር ላይ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያን አባላት ያሉበት ቡድን የ1ኛ ደረጃ አሸናፊ በመሆን የክብር ዲፕሎማ ተሸልሟል።

ቡድኑ "የአየር ንብረት፣ ኤኮሎጂ እና የብዝሃ-ሕይወት ኢንጂነሪንግ" በተሰኘው የሳይንስ ዘርፍ ያቀረበው የፈጠራ ፕሮጀክት አሸናፊ አድርጎታል።

ፕሮጀክቱ "በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የተደገፈ የአካባቢ ጥበቃ ክትትል ሥርዓት ለዘላቂ የማዕድን ማውጣትና የካርቦን ልቀት ክትትል" የተሰኘ ነው። 

ውድድሩ በዩኔስኮ ሥር በሚንቀሳቀሰው የማዕድን ኢንጂነሪንግ ትምህርት ዓለም አቀፍ ማዕከል የተዘጋጀ ሲሆን የወጣቶችን የቴክኖሎጂና የሳይንስ ፈጠራ ለዘላቂ ልማት ለማዋል ያለመ ነው።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0