ህንድ፣ ብራዚል እና ደቡብ አፍሪካ የባሕር ስጋቶችን መግታት ላይ ያነጣጠረ የጋራ የባሕር ወታደራዊ ልምምድ አካሄዱ

ሰብስክራይብ

ህንድ፣ ብራዚል እና ደቡብ አፍሪካ የባሕር ስጋቶችን መግታት ላይ ያነጣጠረ የጋራ የባሕር ወታደራዊ ልምምድ አካሄዱ

​ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 11 የህንድ፣ ብራዚል እና ደቡብ አፍሪካ የባሕር ኃይሎች በደቡብ አፍሪካ አስተናጋጅነት እና በህንድ መሪነት ለሚካሄደው የ (IBSAMAR IX) ልምምድ ኃይሎቻቸውን አቀናጅተዋል።

​በሲሞንስ ታውን እና ፎልስ ቤይ አካባቢ የሚካሄደው ይህ ሥልጠና፤ የባሕር ላይ ወንበዴዎችን፣ ሕገ-ወጥ የዓሣ ጠመዳን፣ የባሕር ሽብርተኝነትን እንዲሁም ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ፣ የአደንዛዥ ዕፅ እና የሰዎች ዝውውርን የመሳሰሉ ስጋቶችን በጋራ ለመከላከል ያለመ ነው።

​ልምምዱ ከወታደራዊ ዝግጁነት ባሻገር የሦስቱ ሀገራት የባሕር ኃይሎች የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ፣ መተማመን እንዲገነቡ እና ግንኙነታቸውን እንዲያሻሽሉ የሚረዳ ነው።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0