- Sputnik አፍሪካ, 1920
The African Heights show
ወቅታዊ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች፣ አዳዲስ መረጃዎች እና በደቡባዊው ዓለም ሀገራት መካከል ጠንካራ ትስስር የሚፈጥሩ አበይት ክስተቶች የሚዳሰሱበት ፕሮግራም።

የሩሲያ-አፍሪካ 3ኛ ጉባኤ፡- ባለብዙ ወገን ዓለምና ስትራቴጂክ አጋርነት​‌

የሩሲያ-አፍሪካ 3ኛ ጉባኤ፡- ባለብዙ ወገን ዓለምና ስትራቴጂክ አጋርነት​
ሰብስክራይብ

"በአዲሱ የዓለም የኃይል ሚዛን ውስጥ አፍሪካ የራሷን ድምፅና ሉዓላዊ ጥቅም ለማስከበር በሞስኮ በሚካሄደው ጉባኤ ላይ የተበታተነ ሳይሆን የጋራ እና የተቀናጀ አህጉራዊ አቋም ይዛ መቅረብ አለባት።"ሲሉ በወልድያ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግኑኝነት መምህር አዲስ አለማየሁ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዚህኛው የአፍሪካን ሃይትስ ዝግጅታችን፦
· ዲፕሎማሲያዊ ትብብርና የዓለም አቀፍ አስተዳደር ተጽዕኖ፦ በብሪክስ መስፋፋትና በባለብዙ ወገን የዓለም አቀፍ አወቃቀር ውስጥ የሩሲያና የአፍሪካ አገራት የፖለቲካ ነፃነት፣ የሉዓላዊነት መከበር እና አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ውስጥ የሚገባትን ውክልና ለማሳደግ የሚደረጉ ጥረቶች፤
· ኢኮኖሚ፣ የኢንዱስትሪ ልማትና የኃይል ደኅንነት፦ የትብብር ስምምነቶችን ከጥሬ ዕቃ ንግድ ወደ ተጨባጭ የኢንዱስትሪ፣ የሥራ ዕድል ፈጠራና የቴክኖሎጂ ሽግግር የመቀየር ዕድሎች፤ እንዲሁም በሰላማዊ የኑክሌርና የታዳሽ ኃይል ልማት የአህጉሪቱን የኢነርጂ ነፃነት የማረጋገጥ ፋይዳ፤
· የደኅንነት፣ የቴክኖሎጂና የወደፊት ስትራቴጂክ አቅጣጫ፦ የአፍሪካን የራስ መከላከያ አቅም የሚያጠናክር የጸጥታ ትብብር፣ በተጨማሪም ከ2026ቱ የሞስኮ ጉባኤ በኋላ የረጅም ጊዜ ተቋማዊና የተጠያቂነት አሠራሮችን የመዘርጋት አስፈላጊነት በወልድያ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግኑኝነት መምህር አዲስ አለማየሁ ጋር በጥልቀትና በስፋት ዳሰነዋል።
ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0