- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል። አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ይህ ፕሮግራምም ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

የአፍሪካ የለውጥ ማዕበል፡ በወጣቶች እጅ እየተቀረጸ ያለው ኃይል እና ተስፋ

የአፍሪካ የለውጥ ማዕበል፡ በወጣቶች እጅ እየተቀረጸ ያለው ኃይል እና ተስፋ
ሰብስክራይብ
አፍሪካ ከህዝቧ 60 በመቶ ያህሉ ከ25 ዓመት በታች የሆነበት በዕድሜ ወጣቷ አህጉር ናት። ይህ ትውልድ የአህጉሪቱን ኢኮኖሚ፣ ፖለቲካ እና በሚለዋወጠው ዓለም አቀፍ ስረዓት ውስጥ የሚኖራትን ስፍራ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀረፀ ይሄዳል።
"አፍሪካ አሁን ተመልካች ብቻ ሳትሆን በልዩ ልዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች ባለድርሻ በመሆኗ ትልቅ ኩራት ይሰማኛል። ድምፃችን የሚሰማ፣ በዕድገት ላይ ያለን እና አሁንም ሊጠናከር የሚገባው አንድነት ያለን ህዝቦች ነን። ብዙ ጉድለቶች ቢኖሩንም፣ አፍሪካዊ ያደረጉን በርካታ ልዩ አዎንታዊ እሴቶች አሉን" ስትል የህግ ባለሙያ፣ ሞዴል እና ስራ ፈጣሪ ሩት ሸዋታጠቅ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግራለች።
በዚህኛው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በፍጥነት በሚለዋወጠው የዓለም ሥርዓት ውስጥ የአፍሪካ ወጣቶችን ሚና እና ተስፋ እንቃኛለን። ይህንንም እውነታ በሕይወት ጎዞዋ ውስጥ ታስመልክተን ዘንድ የህግ ባለሙያ፣ ሞዴል እና ስራ ፈጣሪ ሩት ሸዋታጠቅ እንግዳችን አድርገናል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Deezer – Afripods – Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0