ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ በወታደራዊና የመከላከያ ትብብር ዙሪያ መከሩ

© telegram sputnik_ethiopiaኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ በወታደራዊና የመከላከያ ትብብር ዙሪያ መከሩ
ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ በወታደራዊና የመከላከያ ትብብር ዙሪያ መከሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 15.10.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ በወታደራዊና የመከላከያ ትብብር ዙሪያ መከሩ 

 

የሶማሊላንድ የጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም ብሪጋዴር ጄኔራል ንዕማን የሱፍ ጋህኑግ በሐርጌሳ ከኢትዮጵያ ዲፕሎማቶችና የመከላከያ አታሼዎች ጋር በሁለትዮሽ ወታደራዊ ትብብርና በቀጣናዊ ደህንነት ዙሪያ ተወያይተዋል። 

 

ዋና ዋና ነጥቦች፦ 

 

በሶማሊላንድ የጦር ኃይሎች ዋና መሥሪያ ቤት በተካሄደው ውይይት በሶማሊላንድ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል አምባሳደር ተሾመ እና የመከላከያ አታሼው ተሳትፈዋል። 

 

የኢትዮጵያ ወገን በቅርብ ጊዜያት በቀጣናው ስለታዩ አዳዲስ የደህንነትና የፖለቲካ ሁነቶች ለሶማሊላንድ ወታደራዊ አመራሮች ማብራሪያ ሰጥቷል። 

 

ብሪጋዴር ጄኔራል ንዕማን በሁለቱ ጦሮች መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር በቀጣናው ሰላምና ዘላቂ መረጋጋት ለማስፈን ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል። 

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0