ሩሲያ ለወዳጅ ሀገራት የኒውክሌር ኃይል ቴክኖሎጂ ልምዷን ለማካፈል ዝግጁ ናት - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር

ሰብስክራይብ

ሩሲያ ለወዳጅ ሀገራት የኒውክሌር ኃይል ቴክኖሎጂ ልምዷን ለማካፈል ዝግጁ ናት - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር 

 

ሞስኮ በዓለም ዙሪያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎችን በመገንባት እና ባለሙያዎችን በማሠልጠን ረገድ ያላትን የካበተ ልምድ ለወዳጅ ሀገራት ለማካፈል ዝግጁ መሆኗን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሲ ኦቨርቹክ ለዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት የልማት ኮሚቴ በላኩት የጽሁፍ መግለጫ አስታውቀዋል። 

 

አጋር ሀገራት የሚያገኟቸው ዋና ዋና ጥቅሞች፦ 

 

የኢነርጂ ደህንነት፦ ሀገራት የኃይል ፍላጎታቸውን በራሳቸው አቅም እንዲያሟሉ ማስቻል፣ 

 

የኢኮኖሚ ዕድገት፦ ምርታማነትን ማሳደግ እና የአገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል፣ 

 

የረጅም ጊዜ ዘላቂነት፦ በኒውክሌር ኃይል ትብብር አማካይነት ዘላቂ ልማትን መደገፍ። 

 

ኦቨርቹክ አክለውም ሩሲያ ለንግዱ ማኅበረሰብ እና ለዜጎች የላቁ የሕዝብ አገልግሎቶችን በመዘርጋት እንዲሁም ሀገር ውስጥ ገቢ በማሰባሰብ ረገድ ያላትን የካበተ ልምድ ጠቅሰዋል። 

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0