የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የመድህን ተቆጣጣሪ ኮሚሽን ለማቋቋም የሚያስችል አዲስ አዋጅ እየተዘጋጀ መሆኑን አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopiaየኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የመድህን ተቆጣጣሪ ኮሚሽን ለማቋቋም የሚያስችል አዲስ አዋጅ እየተዘጋጀ መሆኑን አስታወቀ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የመድህን ተቆጣጣሪ ኮሚሽን ለማቋቋም የሚያስችል አዲስ አዋጅ እየተዘጋጀ መሆኑን አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.10.2026
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የመድህን ተቆጣጣሪ ኮሚሽን ለማቋቋም የሚያስችል አዲስ አዋጅ እየተዘጋጀ መሆኑን አስታወቀ  

 

ይህንን በመድህን አገልግሎት ላይ ብቻ ትኩረት የሚያደርግ ኮሚሽን ለማቋቋም የሚያስችለው የመድህን አዋጅ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መላኩን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የቁጥጥር ዳይሬክተር በላይ ቱሉ ለመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ገልጸዋል። 

 

ስለኮሚሽኑ የተባሉ ቁልፍ ነጥቦች፦ 

 

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሲሰጥ የነበረውን አገልግሎት ከተጨማሪ ኃላፊነት ጋር ይዞ በገለልተኝነት የሚቋቋም ይሆናል። 

ለመድህን ተቋማት ፈቃድ ይሰጣል፤ ውጤታማነታቸውንም ይቆጣጠራል፣ ለኢንዱስትሪው ዕድገት በሚበጅ መንገድ እንዲመሩ ጤናማነታቸውን ይቆጣጠራል። 

የመድህን አገልግሎት ጥራትና አይነት ላይ ለማተኮር አጋዥ ይሆናል። 

 

በኢትዮጵያ የመድህን አገልግሎት ለጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት 0.3% ብቻ እንደሚያበረክት ተገልጿል። 

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0