ደቡብ ሱዳን የጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃዎችን ለመዋጋት የዘርፈ ብዙ ተቋማት የጋራ መድረክ ይፋ አደረገች

ሰብስክራይብ

ደቡብ ሱዳን የጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃዎችን ለመዋጋት የዘርፈ ብዙ ተቋማት የጋራ መድረክ ይፋ አደረገች 

 

ደቡብ ሱዳን ምርጫ እና ረቂቅ ሕገ-መንግሥት ለማዘጋጀት እንቅስቃሴ በምታደርግበት በዚህ ወቅት የሰላም ሂደቷን ለማስቀጠልና፣ የጋራ መድረኩን ለመመስረት በጁባ የሦስት ቀን ሀገራዊ ወርክሾፕ በማካሄድ ላይ ትገኛለች። 

 

🟠 ተሳታፊዎች፦ ስብሰባው በምሥራቅ አፍሪካ በይነ-መንግሥታት የልማት ባለሥልጣን (ኢጋድ)፣ በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን እና በተባበሩት መንግሥታት ተቋማት ትብብር አማካኝነት የተካሄደ ሲሆን መንግሥታዊ ተቋማት፣ የሲቪል ማኅበራት እና የሚዲያ ድርጅቶችን ያቀናጀ ነው። 

 

🟠 ምን ያደርጋል፦ በደቡብ ሱዳን የኢጋድ ልዑክ ቡድን መሪ ቪክቶሪያ አኒብ እንደገለጹት፤ መድረኩ ትብብር፣ የመረጃ ልውውጥ እና ለሚከሰቱ አዳዲስ ስጋቶች የተቀናጀ ምላሽ የመስጠት አቅምን ያጠናክራል። 

 

🟠 የጉዳዩ አስቸኳይነት፦ የጥላቻ ንግግር፣ አሉባልታዎች እና የተሳሳቱ መረጃዎች በማኅበረሰቦች መካከል ያለውን እምነት የመሸርሸር እና የፖለቲካ አለመረጋጋት የማስከተል አደጋ እንዳላቸው የተመድ ተወካይ አስጠንቅቀዋል። አዲሶቹ እርምጃዎች የመናገር ነፃነት እና ነጻ ፕሬስን የሚጎዱ መሆን እንደሌለባቸው አስምረውበታል። 

 

🟠 ቀጣይ እርምጃዎች፦ ተሳታፊዎቹ የተቋማትን ድርሻ ይወስናሉ፤ ቅድመ-ማስጠንቀቂያ ዘዴዎችን ከቅድመ-መከላከል እርምጃዎች ጋር ያጣጥማሉ እንዲሁም የመድረኩን ሀገራዊ ባለቤትነት ያጠናክራሉ ተብሎ ይጠበቃል። 

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0