አውሮፓውያን ሀገራት የሩሲያ-አሜሪካ ስምምነቶችን የማደናቀፍ ስጋት ደቅነዋል - ክሬምሊን
17:05 14.10.2026 (የተሻሻለ: 17:14 14.10.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
አውሮፓውያን ሀገራት የሩሲያ-አሜሪካ ስምምነቶችን የማደናቀፍ ስጋት ደቅነዋል - ክሬምሊን
"በአውሮፓ ሀገራት በኩል የማደናቀፍ ስጋቶች አሉ። አሜሪካ፤ የአሜሪካ ተደራዳሪዎች እና ፕሬዚዳንት ትራምፕ በዩክሬን ዙሪያ ያለውን ቀውስ ወደ ሰላማዊ ጎዳና ለመምራት ጥረቶችን እያደረጉ ነው። አውሮፓውያን ግን ከዚህ የተለየ አካሄድ እየተከተሉ ይገኛሉ፤ ጦርነቱ እንዲቀጥል የሚቻላቸውን እያደረጉ ነው" ሲሉ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ተናግረዋል።
ቃል አቀባዩ ያነሷቸው ተጨማሪ ነጥቦች፦
ክሬምሊን በሚዲያ ከሚነገረው ውጭ የስታርሊንክ አገልግሎት በዩክሬን ስለመታገዱ የሚያውቀው ነገር የለም።
እንደ ስታርሊንክ ያሉት ቴክኖሎጂዎች ለጦርነት ዓላማዎች ባይውሉ የተሻለ ነው።
እስካሁን በዩክሬን የሰላም ሂደት ዙሪያ ዓለም አቀፍ ስብሰባ ለማካሄድ የተደረሰ ስምምነት የለም።
ሩሲያ ንብረቶቿን ለማስመለስ መታገሏን ትቀጥላለች።
የሩሲያ የፌዴራል ደህንነት አገልግሎት ተግባራቱን እያከናወነና ሰላዮችን እየያዘ ይገኛል።
ሩሲያ በሳይበር ደህንነት ግንባር ለሚከሰቱ ተግዳሮቶች ዝግጁ መሆን አለባት።
ፕሬዚዳንት ፑቲን ዛሬ በሳይበር ደህንነት ዙሪያ ስብሰባ ያደርጋሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X