ሩሲያ ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማጋራትና የኢትዮጵያን የማምረት አቅም ለማሳደግ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት - በኢትዮጵያ የሩሲያ የንግድ ተወካይ
21:03 13.10.2026 (የተሻሻለ: 21:04 13.10.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያ ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማጋራትና የኢትዮጵያን የማምረት አቅም ለማሳደግ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት - በኢትዮጵያ የሩሲያ የንግድ ተወካይ
ያሮስላቭ ታራስዩክ፤ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከሩሲያ ጋር ከፍተኛ የንግድ ልውውጥ ካላቸው 10 ዋና ዋና ሀገራት መካከል አንዷ መሆኗን ከሀገር ውስጥ ሚዲያ ጋር በነበራቸው ቆይታ አመልክተዋል።
ቁልፍ ነጥቦች፦
በ2025 የሁለቱ ሀገራት የንግድ ልውውጥ ከፍተኛ መነቃቃት አሳይቷል፣
ሩሲያ ወደ ኢትዮጵያ የምትልከው ምርት በአራት እጥፍ አድጓል፣ ኢትዮጵያ ወደ ሩሲያ የምትልከው ምርት በእጥፍ ጨምሯል፣
ኢትዮጵያ ቡና፣ አበባ፣ ፍራፍሬ፣ አትክልት፣ አቮካዶ፣ ቅጠላ ቅጠሎችና ሌሎች የግብርና ምርቶችንም ወደ ሩሲያ ልካለች፣
ሩሲያ በበኩሏ እንደ ማዕድን ማዳበሪያና የሱፍ ዘይት ያሉ ቁልፍ ምርቶችን ለኢትዮጵያ ታቀርባለች።
ታራስዩክ፤ ትብብሩ ከተለመደው የንግድ ልውውጥ ባሻገር የጋራ ኢንቨስትመንት፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም የግብርና ማሽኖችና ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ ማምረትን ማካተት እንዳለበት አስገንዝበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X