"በኪዳል አንቆምም" - ቁልፏን ከተማ ከተቆጣጠሩ በኋላ የማሊ ሠራዊት ኤታ ማዦር ሹም የተናገሩት
20:26 13.10.2026 (የተሻሻለ: 20:34 13.10.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
"በኪዳል አንቆምም" - ቁልፏን ከተማ ከተቆጣጠሩ በኋላ የማሊ ሠራዊት ኤታ ማዦር ሹም የተናገሩት
ማሊ ኪዳልን ከሽብርተኞች ቁጥጥር ስር ከነጠቀች አንድ ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ፤ የማሊ ሠራዊት ሜጀር ጄኔራል ዣን ኤሊዜ ዳኦ ሁኔታውን ለመገምገም እና በዘመቻው የተሳተፉትን ክፍሎች ለማመሥገን አካባቢውን ጎብኝተዋል።
ጄኔራሉ የቀሩትን የታጠቁ ቡድኖች ለመደምሰስ በሌሎች አቅጣጫዎችም ዘመቻዎች እንደሚቀጥሉ አፅንዖት ሰጥተዋል።
የሠራዊቱ ኃይሎች ባለፈው ግንቦት ወር መጀመሪያ ከከተማው ከወጡበት ጊዜ ጀምሮ ሠራዊቱ ወደ ቦታው ለመመለስ ሲዘጋጅ እንደነበር እና ጥቃቱን ከመፈጸሙ በፊት የጠላትን ሎጂስቲክስና ጦር መሣሪያ አቅም የማዳከም ስትራቴጂ እንደተከተለ ጄኔራሉ አስታውሰዋል።
ጄኔራሉ የሰው ሕይወት ኪሳራን እንዲቀንስ ያስቻለውን እቅድ አውድሰው፤ አካባቢያዊ እና ስትራቴጂካዊ አጋሮችን በተለይም የሩሲያ ጦር አፍሪካ ኮር ላደረገው ድጋፍ ምሥጋና አቅርበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X