አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ በፎርብስ አፍሪካ 15 አርአያ አፍሪካውያን ተርታ ውስጥ ተካተተ
19:41 13.10.2026 (የተሻሻለ: 19:44 13.10.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ በፎርብስ አፍሪካ 15 አርአያ አፍሪካውያን ተርታ ውስጥ ተካተተ
መጽሔቱ 15ተኛ ዓመቱን በማስመልከት ይፋ ባደረገው ዝርዝር ውስጥ ሃሳባቸው፣ ድምጻቸው እና ሥራቸው በአፍሪካ አኅጉር ያለፈ፣ የአሁን እና የወደፊት እጣ ፈንታ ላይ አዎንታዊና ዘላቂ ተፅዕኖ ማሳደር የቻሉ አፍሪካውያንን አካቷል።
በስፖርት እና ስኬታማ ንግድ ዘርፍ ስሙ የተጠቀሰው አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ፦
ሁለት የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያዎች፣
ስምንት የዓለም ሻምፒዮናዎች፣
27 የዓለም ሪከርዶችን መስበሩ በስፖርት ዘርፉ የተጠቀሱ የተጎናፀፋቸው ድሎች ናቸው።
በንግድ መስክ፤ በ "ኃይሌ እና አለም ኢንተርናሽናል" ኩባንያ ስር በሆቴል፣ በመኪና ማምረቻ፣ በሪል እስቴት እና ግብርና ዘርፎች ተሠማርቶ ያገኘው ስኬት በዝርዝሩ ውስጥ እንዲካተት አስችሎታል።
አሊኮ ዳንጎቴ፣ የቀድሞዋ የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ፣ የዓለም ንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ንጎዚ ኦኮንጆ-ኢዌላ እንዲሁም የቀድሞው የኮትዲቯር እና ቼልሲ አጥቂ ዲዲዬር ድሮግባ በዝርዝሩ ውስጥ የተካተቱ ሌሎች ጉልህ አፍሪካውያን ናቸው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X