የዩክሬን ወታደራዊ እርምጃዎች የአሜሪካን ጥቅም ከጎዳ ለኪየቭ የሚደረገው ድጋፍ እንዲቀንሰ ያደርጋል - ቻይናዊ ተንታኝ
18:59 13.10.2026 (የተሻሻለ: 19:04 13.10.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የዩክሬን ወታደራዊ እርምጃዎች የአሜሪካን ጥቅም ከጎዳ ለኪየቭ የሚደረገው ድጋፍ እንዲቀንሰ ያደርጋል - ቻይናዊ ተንታኝ
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት በቅርቡ በዩክሬን አዲስ መሪ እንዲመጣ ባቀረቡት ጥሪ፤ ከዩክሬን ጉዳይ ይልቅ "ቅድሚያ ለአሜሪካ" አጀንዳቸውን በማስበለጥ ፖለቲካዊ ጫና እያሳደሩ ነው ሲሉ የፖለቲካ ተንታኙ ዦው ቸንግያንግ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
ትራምፕ በተለይም ከአሜሪካ የአካፋይ ምርጫ በፊት ለሀገር ውስጥ ጉዳዮች ትኩረት ስለሚሰጡ፤ ለዩክሬን የሚደረገው ድጋፍ የማይቀየር ነው ማለት እንዳልሆነ የሚያሳይ ነው ሲሉ ተንታኙ ገልጸዋል።
ትራምፕ በተራዘመው ምርጫ ምክንያት የዘለንስኪን ሕጋዊነት ጥያቄ ውስጥ መክተታቸው፤ በዋሽንግተን እና በኪየቭ መካከል እምነት መሸርሸሩን የሚያሳይ ቢሆንም ይህ ፖለቲካዊ ጫና ለዘለንስኪ ሀገር ውስጥ የበለጠ ድጋፍ ሊያስገኝለት እንደሚችል አፅንዖት ሰጥተዋል።
በተጨማሪም ጀርመን፣ እንግሊዝ እና ፈረንሳይን ጨምሮ የአውሮፓ ሀገራት ለዘለንስኪ ድጋፋቸውን ዳግም ማረጋገጣቸው፤ በዋሽንግተን እና በአውሮፓ ወዳጆቿ መካከል ግልጽ ልዩነት እንዳለ ያሳያል ሲሉ ባለሙያው አክለዋል።
ቪዲዮው ትራምፕ ዘለንስኪ ስምምነት ለማድረግ ፍላጎት እንደሌለው ለጋዜጠኞች ሲናገሩ ያሳያል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X