የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለኃይል ዘርፍ ማዘመኛ የሚውል የ145.8 ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት አጸደቀ
18:43 13.10.2026 (የተሻሻለ: 18:44 13.10.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለኃይል ዘርፍ ማዘመኛ የሚውል የ145.8 ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት አጸደቀ
ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ያፀደቀዉ አዲስ ብድር፤ የኢትዮጵያ መንግሥት እና የዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር የተፈራረሙት የኃይል ዘርፉ ማሻሻያ ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ ምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል ነው።
ቁልፍ ነጥቦች፦
ብድሩ ቀላልና አነስተኛ የገንዘብ ጫና የሚፈጥር ነው ተብሏል።
የ6 ዓመት የእፎይታ ጊዜን ጨምሮ በ31 ዓመታት ውስጥ ተከፍሎ የሚጠናቀቅ ነው።
ብድሩ የአዲስ አበባን የኃይል ማስተላለፊያ መረብ ለማጠናከር፣ አዳዲስ የኃይል ጣቢያዎችን ለመገንባትና ነባሮቹን ለማሻሻል እንዲሁም የመሬት ውስጥ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን ለመዘርጋት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X