ብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን እስካሁን ከ92 ሺህ በላይ የቀድሞ ተዋጊዎች እንደገና መቋቋማቸውን አስታወቀ
16:21 13.10.2026 (የተሻሻለ: 16:24 13.10.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን እስካሁን ከ92 ሺህ በላይ የቀድሞ ተዋጊዎች እንደገና መቋቋማቸውን አስታወቀ
የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ ማስፈታት፣ መበተንና መልሶ የማቋቋም ፕሮግራም አተገባበር ተጠናክሮ መቀጠሉን የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን ገልጸዋል።
በትግራይ ክልል በርካታ ተዋጊዎች ግጭትን ትተው ወደ ሰላማዊ ህይወት ለመመለስ ወደ ተሃድሶ ማዕከላት ለመግባት ከፍተኛ ፍላጎት እያሳዩ መሆኑንም አስታውቀዋል።
ኮሚሽኑ በክልሉ ትጥቅ የማስፈታት፣ የመበተንና መልሶ የማቋቋም ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል፤ በአዲስ መልክ በተመረጡ ተጨማሪ ጊዜያዊ የተሃድሶ ማዕከላት የቀድሞ ተዋጊዎችን ለመቀበልና ለማሠልጠን ዝግጅት አጠናቅቂያለሁ ብሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X