አቡጃ በ "የናይጄሪያ ልዑል" የድረ-ገፅ አጭበርባሪዎች ላይ ጥብቅ እርምጃ መውሰድ ጀመረች

ሰብስክራይብ

አቡጃ በ "የናይጄሪያ ልዑል" የድረ-ገፅ አጭበርባሪዎች ላይ ጥብቅ እርምጃ መውሰድ ጀመረች

በሞስኮ ከተካሄደው ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የዲጂታል መድረክ ጎን ለጎን ከስፑትኒክ ጋር ቆይታ ያደረጉት የናይጄሪያ የፈጠራ፣ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚንስትር ኪንግስሊ ቶቹክዉ ኡዴ፤ ባለሥልጣናት የውጭ ዜጎችን በትላልቅ ርስት እና ውርስ ተስፋ የሚያታልሉ አጭበርባሪዎችን እየፈለጉ፣ እያሠሩ እና ለፍርድ እያቀረቡ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

የሕግ አስከባሪ አካላት አጭበርባሪዎችን በመከታተል ረገድ ይበልጥ ውጤታማ መሆን እንደጀመሩ ጠቅሰው፤ የኢኮኖሚ እና የፋይናንስ ወንጀሎች ኮሚሽን እነዚህን አካላት ለፍርድ ለማቅረብ የሚደረገውን ጥረት እየመራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

 

“ይህ ለሀገራችን ገጽታ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ እናውቃለን” ሲሉ አፅንኦት ሰጥተዋል።

'የናይጄሪያ ልዑል' ማጭበርበር ምንድን ነው?

ተጎጂዎች ትልቅ ሀብት እንደሚያገኙ ቃል በመግባት፤ አስቀድመው ክፍያዎችን እንዲከፍሉ የሚጠይቅ ለብዙዎች መታለል ምክንያት የሆነ የማጭበርበር ዓይነት ነው። ተጎጂዎች ብሩን ከላኩ በኋላ እንኳን አጭበርባሪዎቹ ተጨማሪ ገንዘብ የሚጠይቁበት ሁኔታ የተለመደ ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0