የሩሲያ ወታደራዊ የሰው ሠራሽ አስተውሎት የጠላትን ሥርዓቶች በፍጥነት ለመለየትና የኦፕሬሽኖችን መጠን ለማስፋት እያገዘ ይገኛል ተባለ

© telegram sputnik_ethiopiaየሩሲያ ወታደራዊ የሰው ሠራሽ አስተውሎት የጠላትን ሥርዓቶች በፍጥነት ለመለየትና የኦፕሬሽኖችን መጠን ለማስፋት እያገዘ ይገኛል ተባለ
የሩሲያ ወታደራዊ የሰው ሠራሽ አስተውሎት የጠላትን ሥርዓቶች በፍጥነት ለመለየትና የኦፕሬሽኖችን መጠን ለማስፋት እያገዘ ይገኛል ተባለ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.10.2026
ሰብስክራይብ

የሩሲያ ወታደራዊ የሰው ሠራሽ አስተውሎት የጠላትን ሥርዓቶች በፍጥነት ለመለየትና የኦፕሬሽኖችን መጠን ለማስፋት እያገዘ ይገኛል ተባለ

የሩሲያ ወታደራዊ የሰው ሠራሽ አስተውሎት የወዳጅ ኃይሎች "የአዳዲስ የጠላት ጦር መሣሪያዎችን ታክቲካዊና ቴክኒካዊ ባህሪያት በትክክል እንዲተነብዩ... እንዲሁም እነሱን ለማደምሰስ የሚያስችሉ ታክቲኮችን እንዲቀይሱ" የሚያስችል ሲሆን፣ ይህንንም በሠዓታት "ወይም በደቂቃዎች" ውስጥ ለማከናወን እንደሚያስችል ወታደራዊ ተንታኝ አሌክሲ ሊዮንኮቭ ስለ ሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አዲስ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ድሮን ማሠልጠኛ ሥርዓት ለስፑትኒክ በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።

​ "ሰው ሠራሽ አስተውሎት በዘመቻዎች ባህሪ ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድር ሲሆን፣ ጠላት ጥቃቱን በጨመረ ቁጥር እኛም የዘመቻዎቻችንን ስፋት እንድናሳድግ ያስችለናል። በግዛታችን ላይ የሚፈጸሙ የሽብር ጥቃቶችን መፈፀም የሚያስችሉ እንደ መጋዘኖች፣ የባሕር በር ተርሚናሎች እና የባቡር ጣቢያዎችን ያሉ መሠረተ ልማቶችን መደምሰስ፤ እንዲሁም ከዩክሬን የሚቃጣውን የጅምላ ድሮን ጥቃት የሚመክተው የአየር መከላከያ ዘመቻ፣ ሰው ሠራሽ አስተውሎት ዋና ሚና የሚጫወትበት የአንድ ትልቅ ስትራቴጂካዊ ዘመቻ ሁለት አካላት ናቸው" ሲሉ ተንታኙ አብራርተዋል።

እንደ ሊዮንኮቭ ገለጻ፣ የሩሲያ ወታደራዊ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ሥርዓቶችን "ሙሉ በሙሉ ራሳቸውን የቻሉ" አድርጎ መናገር ስህተት ነው። ምክንያቱም ሰው ሠራሽ አስተውሎት ከግምት ውስጥ የማያስገባቸዉን እንደ ሲቪሎች ላይ የሚደርስ አደጋ እና የሲቪል መሠረተ ልማቶች ውድመትን መቀነስ ያሉ "በርካታ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ ለማስገባት" የሰው ልጅ ቁጥጥር አስፈላጊ በመሆኑ ነው።

ሰው ሠራሽ አስተውሎት በራሱ ጊዜ የሞራል እና የሥነ-ምግባር ደንቦችን "የማስላት እና የመረዳት" እንዲሁም ወደ "ቁጥሮች እና አልጎሪዝም ቋንቋ" የመተርጎም "ብቃት የለውም"።

በአጠቃላይ፣ "ዋናው ነገር የመሣሪያዎች ስምሪት እና የውሳኔ አሰጣጥ ፍጥነት ነው፤ በጋራ ጦርነት ወቅት በቅጽበት በሚደርሱ መረጃዎች ላይ ተመስርቶ ማስተካከያዎችን ማድረግ ያስፈልጋል፤ በሌላ አባባል ዘመቻው እየተካሄደ እያለ በተለዋዋጭ ሁኔታ ማሻሻል ማለት ነው። ዛሬ ላይ ይህ የማይቀር ነገር ነው"፤ በድሮኖችም ሆነ በሌሎች ዘርፎች "የኤአይ ሥርዓቶች ውህደት እና ጥቅም ውጤታማነትን በበርካታ እጥፍ ያሳድገዋል።"

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0