ሶማሊያ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ያለው ውጥረት እያየለ መምጣቱን ተከትሎ ገለልተኛ መሆኗን አስታወቀች
18:15 12.10.2026 (የተሻሻለ: 18:24 12.10.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሶማሊያ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ያለው ውጥረት እያየለ መምጣቱን ተከትሎ ገለልተኛ መሆኗን አስታወቀች
ሶማሊያ ከግብፅ እና ከሌሎች የቀጣናዊ ኃይሎች ጋር እያደገ በመጣው ትብብር በግጭቱ ውስጥ ወደ አንድ ወገን አድልታለች የሚሉ ግምቶችን አስተባብላለች።
ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሀሰን ሞሃመድ አሊ ናዳራ እንደተናገሩት፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ያገረሸረው ውጊያ ወደ ሰፊ ቀጣናዊ ግጭት ሊያመራ ይችላል የሚል ስጋት ቢኖርም፣ ሞቃዲሾ በጉዳዩ ላይ ከተሳተፉት ሀገራት ሁሉ ጋር ላላት ሰላማዊ ግንኙነት ቁርጠኛ ሆና ትቀጥላለች።
የሚኒስትሩ አስተያየት የተሰማው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ በግብፅ፣ ኤርትራ እና ሱዳን መሪዎች ጉባኤ ላይ ከተሳተፉ ከሳምንት በኋላ ሲሆን፣ ይህም በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ እያደገ በመጣው ክፍፍል መካከል በሶማሊያ አቋም ላይ ጥያቄዎችን አስነስቶ ነበር።
ከኢትዮጵያ ጋር ረጅም የየብስ ወሰን የምትጋራው እና ከአዲስ አበባ ጋር የፀጥታ ትብብር ያላት ሶማሊያ፣ ከሁሉም ወገኖች ጋር ያላትን ግንኙነት ጠብቃ ለመቀጠል እየጣረች ትገኛለች ሲሉ የሱማሊያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X