የፑንትላንድ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት የቀጣናው ውጥረት ባየለበት ወቅት ከኢትዮጵያ ቆንስላ ጄነራል ጋር ተወያዩ
15:35 12.10.2026 (የተሻሻለ: 15:44 12.10.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የፑንትላንድ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት የቀጣናው ውጥረት ባየለበት ወቅት ከኢትዮጵያ ቆንስላ ጄነራል ጋር ተወያዩ
የፑንትላንድ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንት ኢልያስ ኦስማን ሉጋቶር፣ በጋሮዌ ከሚገኙት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄነራል ብርጋዴር ጄነራል ታገሠ ላምባሞ ዲምቦሬ እና ከሌሎችን የቆንስላው ባለሥልጣናትን ጋር መወያየታቸውን አስታውቀዋል።
የውይይቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
የትብብር መስኮች፦ ሁለቱ ወገኖች በደህንነት፣ በንግድ እና በኢኮኖሚ ልማት ዙሪያ አብረው ስለሚሰሩባቸው መንገዶች መክረዋል።
ግንኙነትን ማጠናከር፦ በፑንትላንድ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር እና የጠበቀ ቅንጅት መፍጠር ላይ ትኩረት ተደርጓል።
ይህ ውይይት የተካሄደው ኢትዮጵያ ከኤርትራ፣ ከግብጽ እና ከሱዳን ጋር በባሕር በር ጥያቄ እና በዓባይ ወንዝ አጠቃቀም ዙሪያ ውጥረት ውስጥ በገባችበት ወቅት ነው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X