ሩሲያ እና ቻይና በዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ውድድር የአሜሪካን የበላይነት እየተገዳደሩ ነው - ባለሙያ

ሩሲያ እና ቻይና በዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ውድድር የአሜሪካን የበላይነት እየተገዳደሩ ነው - ባለሙያ
ማይክሮቺፕስ፣ ወሳኝ ማዕድናት እና የአልጎሪዝም ውድድር በሀገራት መካከል ያለው የጂኦፖለቲካዊ ውድድር አካል እየሆነ በመጣበት በዚህ ወቅት፣ ዲጂታላይዜሽን የብሔራዊ ኃይል መሣሪያ መሆኑን ብራዚላዊው ባለሙያ አሌክሳንደር ፔሬዝ ለስፑትኒክ ገልጸዋል።
ባለሙያው የአሜሪካን ቦታ በዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ውድድር ለማጠናከር ያለመውንና ከጂኦፖለቲካዊ ተፎካካሪዎቿ ጋር ያለውን ውጥረት የሚያበብሰው "ፓክስ ሲሊካ" የተሰኘውን በአሜሪካ የሚመራውን እንቅስቃሴ ጠቅሰዋል።
ሩሲያ እና ቻይና በምዕራባውያን ማዕቀቦች ውስጥም ሆነው የራሳቸውን የረቀቁ ቴክኖሎጂዎች ማልማት የጀመሩ ሲሆን፣ ይህም የበለጠ ሉአላዊነትን ለሚፈልጉ የደቡባዊ ዓለም ሀገራት አማራጭ የመሆን አቅማቸውን እያጠናከረ ይገኛል ሲሉ ፔሬዝ ጠቁመዋል።
ሞስኮ እና ቤጂንግ በተጨማሪም፣ "ብዙ ማዕከል ያላትን ዓለም ማስተዋወቅ እና አሜሪካ ብቻዋን በዓለም ላይ የሚከሰተውን ነገር የምትቆጣጠርበት የነጠላ ኃይል የበላይነት እንዳይፈጠር ማድረግን በመሳሰሉ በርካታ ጉዳዮች ላይ የጋራ አቋም አግኝተዋል።"
ፔሬዝ፣ "ከምዕራባውያን ሀገራት እና ከምዕራቡ ስትራቴጂካዊ ወዳጆች፣ ባሻገር በዓለም ዙሪያ ካሉ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጫዋቾች ጋር ዘላቂ የብዙ ወገን ትብብርን ለሚያስቀድመው" የዓለም የሰው ሠራሽ አስተውህሎት ትብብር ድርጅት ቻይና የምታደርገውን መሪነት አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
ባለሙያው በተጨማሪም፣ "ፒክስ" በተሰኘው የቅጽበታዊ ክፍያ ስርዓቷ ስኬት በዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ውድድር ውስጥ "እየጨመረ የሚሄድ አወንታዊ ሚና መጫወት የጀመረችውን" ብራዚልን ጠቅሰዋል።
"እስኪ የነዚህን ቴክኖሎጂዎች ስትራቴጂካዊ ስፋት እንደገና እንመልከት። ትራምፕ የፒክስ ስርዓት የአሜሪካ ኩባንያዎችን ይጎዳል በሚል አሳብ በብራዚል ላይ ማዕቀብ ለመጣል ከጠቀሷቸው ዋና ዋና ምክንያቶች አንዱ የፒክስን አጠቃቀም ነው" ሲሉ ፔሬዝ አጠቃልለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X