የሩሲያ እና የአፍሪካ ታሪካዊ ግንኙነት የበለጠ የማጠናከሪያ ጊዜ መጥቷል - ኢትዮጵያዊ የታሪክ ተመራማሪ
የሩሲያ እና የአፍሪካ ታሪካዊ ግንኙነት የበለጠ የማጠናከሪያ ጊዜ መጥቷል - ኢትዮጵያዊ የታሪክ ተመራማሪ
የታሪክ ተመራማሪው አሕመድ ዘካሪያ “ሩሲያ፦ የአፍሪካን አስተዳደር ለማሻሻል የሀገር በቀል ፍልስፍናዎችን መጠቀም” በሚል ርዕስ ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጡት ቃለመጠይቅ፤ ሩሲያ ከአፍሪካ አኅጉር ጋር ያላት ታሪካዊ ግንኙነት ዝምድና፣ መልክዓ–ምድር ያልገደበው ጉርብትና እንደገና የሚመሠረትበትን ሁኔታ እያየን ብለዋል።
ተመራማሪው “... (ወቅቱ) በዓለም አቀፍ ደረጃም ቢሆን አንድ ጌታ ሁሉንም አስተዳድራለሁ ብሎ የሚገዛበት ጊዜ እያከተመ የሄደበት ነው። የአንድ ዘውግ ሥርዓት ተዳክሞ ብዙ ዘውጎች የሚመጡበትን ሁኔታ እያየን ነው።” ሲሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ አዳዲስ ሁነቶች እየተፈጠሩ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡
በአጠቃላይ ሩሲያ አፍሪካ ውስጥ ቅኝ ግዛት ያልነበራት ሀገር መሆኗን የጠቀሱት ተመራማሪው፣ የሶሻሊዝም ጎራ መዳከሙ የነበረውን ሁኔታ በመጠኑም አዛብቶት እንደነበረ ገልፀው፤ ዛሬ ላይ ግን ባለብዝኃ–ዋልታ ዓለም እየተመሠረተ መሆኑን አጽናኦት ሰጥተዋል፡፡
ስለ ኢትዮ–ሩሲያ ታሪካዊ ወዳጅነት የጠቀሷቸው ቁልፍ ነጥቦች፦
የኢትዮጵያና ሩሲያ ታሪካዊ ትብብር፦ የካራማራው ድል እና የባሕር ዳር ፖሊቴክኒክ ኢንስቲትዩት ግንባታ የሩሲያ (የቀድሞ ሶቪዬት ኅብረት) ትልቅ የድጋፍ ማሳያዎች ናቸው።
በሰው ኃይል ልማት ያበረከተችው አስተዋጽኦ፦ በ17ቱ ዓመታት የሶሻሊዝም ሥርዓት ወቅት በርካታ ኢትዮጵያውያንና አፍሪካውያን በሩሲያ በትምህርት፣ በምህንድስና እና በሕክምና ዘርፍ ሰልጥነው ለሀገራቸውና ለዓለም አበርክተዋል።
ግንኙነትን የማደስ አስፈላጊነት፦ ቀደም ሲል የነበረውን አጋርነትና ወንድማማችነት መሠረት በማድረግ የአሁኑን ግንኙነት የበለጠ የማጠናከሪያ ጊዜው አሁን መሆኑ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X