የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለካርቦን ልቀት ማካካሻ 6 ሚሊዮን ዶላር መክፈሉን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገለጹ

ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለካርቦን ልቀት ማካካሻ 6 ሚሊዮን ዶላር መክፈሉን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገለጹ

 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው የዓለም አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ሕጎችና የመንግሥታት ግብር መጨመር በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ላይ ከፍተኛ የፋይናንስ ጫና እያሳደሩ መሆናቸውን በአዲስ አበባ በተካሄደው 4ኛው የምስራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ የውስጥ የሕግ አማካሪዎች ጉባኤ ላይ መናገራቸውን የሀገር ውስጥ የግል ሚዲያ ዘግቧል።

 

አየር መንገዱ በ2025/26 በጀት ዓመት ብቻ ለካርቦን ማካካሻ (ካርቦን ክሬዲትስ) 6 ሚሊዮን ዶላር የከፈለ ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (አይሲኤኦ) የዓለም አቀፍ አቪዬሽን የካርቦን ቅነሳና ማክካሻ ዕቅድ (ሲኦአርኤስአይኤ) ማዕቀፍ መሠረት ይህ ክፍያ ወደፊት እንደሚጨምር አመላክተዋል።

 

 የዋና ሥራ አስፈጻሚው የጠቀሷቸው ዓለም አቀፍ አሳሳቢ ተግዳሮቶች፦

 

🟠የሕጎ ቁጥጥር መበታተን፦ በአይሲኤኦ የተዘረጋው ሲኦአርኤስአይኤ የተቀናጀ የዓለም አቀፍ ደንብ እያለ፣ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ተጨማሪና የተበታተኑ የካርቦን ክፍያዎችን መጣላቸው የኢንዱስትሪውን ጫና አብዝቶታል።

🟠የዘላቂ አቪዬሽን ነዳጅ (ሳፍ) እጥረት፦ ዘላቂ ነዳጅን ከተራው ነዳጅ ጋር ቀላቅሎ መጠቀም መፍትሔ ቢሆንም፣ በአፍሪካ አህጉር በፍጹም ስለማይገኝና ከፍተኛ ዋጋ ስላለው የመጠቀም ዕድሉ መገደቡን ገልጸዋል።

 

🟠የደንበኞች መብት ሕጎች ጫና፦ በኤውሮፓ እና በሰሜን አሜሪካ የሚተገበሩት ውስብስብ የደንበኞች መብት ጥበቃ ሕጎች በዓለም አቀፍ አየር መንገዶች ላይ የሕግ ተከታታይነትና የወጪ ጫና ፈጥረዋል።

 

🟠ያልተጠበቁ ግብሮች፦ በመላው ዓለም ያሉ መንግሥታት የሚጥሏቸው ግብሮች እየጨመሩ ሲሆን፣ በአንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት እስከ 1970 (እ.ኤ.አ) ድረስ ወደኋላ ተመልሰው ያልተለመዱ የታክስ ጥያቄዎችን እንደሚያቀርቡ ጠቁመዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0