ሩሲያ እና አሜሪካ ወደፊት እንደገና ሊገናኙ ይችላሉ ሲሉ ጂኦሎጂስቶች ተነበዩ
15:59 11.10.2026 (የተሻሻለ: 16:04 11.10.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያ እና አሜሪካ ወደፊት እንደገና ሊገናኙ ይችላሉ ሲሉ ጂኦሎጂስቶች ተነበዩ
የምድር ገጽ ከዚህ ቀደም ይገመት ከነበረው በላይ በፍጥነት እየተለወጠ መሆኑን ሳይንቲስቶች አረጋግጠዋል። በጥናት እንደተመለከተው፣ አኅጉራቱ ከሁለት መቶ እስከ ሦስት መቶ ሚሊዮን ዓመታት ውስጥ ዳግም በመቀላቀል አንድ ግዙፍ አኅጉር ሊፈጥሩ ይችላሉ።
ይህ ሊሆን የሚችለው በአትላንቲክ ውቅያኖስ ቀስ በቀስ መዘጋት አማካይነት ነው። በዚህም የተነሣ አኅጉራቱ ወደ ሰሜናዊው ንፍቀ ክበብ ይሰበሰባሉ፤ ዩሬሺያም በባይካል ሐይቅ አካባቢ ባለው ሰንጠረዥ ለሁለት ትከፈላለች።
በዚህ መልክ ሩሲያ ከሰሜን አሜሪካ ጋር መልሳ ልትገናኝ ትችላለች።
አኅጉራት በአሁኑ ወቅት የምድር መካከለኛ ንብርብር ላይ በሚንሸራተቱ ፕሌቶች አማካይነት ይንቀሳቀሳሉ። ይህ የመራራቅና የመሰባበር ዑደት በየአራት መቶ እስከ ስድስት መቶ ሚሊዮን ዓመታት ይደገማል።
እነዚህ ለውጦች በምሥራቅ አፍሪካ በግልጽ እየታዩ ነው፤ አኅጉሪቱ ለሁለት እየተከፈለች ትገኛለች። በኬንያ የቱርካና ቀጣና ላይ የሚታየው የመሬት ቅርፊት መቅጠን የምሥራቅ አፍሪካ የስምጥ ሸለቆ ለመሰነጣጠቅ እየተዘጋጀ መሆኑን ያሳያል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X