መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጅታል አግልግሎት በአዲስ አበባ የ99.6 በመቶ የተገልጋይ እርካታ ማስመስገቡ ተገለጸ
14:15 11.10.2026 (የተሻሻለ: 14:24 11.10.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጅታል አግልግሎት በአዲስ አበባ የ99.6 በመቶ የተገልጋይ እርካታ ማስመስገቡ ተገለጸ
ተገልጋዮች በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ቀጥተኛ ተሳትፍና ባለቤትነት እንዲኖራቸው በተዘረጋው አሠራር ሌብነትንና ብልሹ አሠራርን በመቀነስ ግልጽነትና ተጠያቂነትን የሚያሰፍን መሠረት መጣሉን የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቤሩ አስታውቋል።
ዋና ዋና ነጥቦች፦
እርካታ፦ 1 ሚሊዮን ተገልጋዮችን አስተናግዶ 99.6% የተገልጋይ እርካታ ተመዝግቧል።
ተደራሽነት፦ በዋናው መሥሪያ ቤትና በ11ዱም ክፍለ ከተሞች አገልግሎት እየተሰጠ ነው።
ዲጂታል ማሻሻያ፦ 392 ዲጂታል አገልግሎቶች ፀድቀው ሥራ ላይ የዋሉ ሲሆን፣ ተጨማሪ 324 ተለይተዋል።
በ2019 ሩብ ዓመት የተለዩ 30 ዋና ዋና አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ ወደ ትግበራ ገብተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X