የብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን ወደ ኅብረተሰቡ መቀላቀል ለሚሹ የሕወሓት ታጣቂዎች የተዘጋጁ የተሃድሶ ማዕከላትን ይፋ አደረገ
12:05 11.10.2026 (የተሻሻለ: 12:14 11.10.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን ወደ ኅብረተሰቡ መቀላቀል ለሚሹ የሕወሓት ታጣቂዎች የተዘጋጁ የተሃድሶ ማዕከላትን ይፋ አደረገ
የብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ብርጋዴር ጄኔራል ደርቤ መኩሪያው፣ በሕወሓት ውስጥ ያለ አንድ አንጃ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት በማናጋት፣ የትጥቅ መፍታት እና የተሃድሶ ሂደቱን በማደናቀፍ እንዲሁም ተጨማሪ ወጣቶችን ወደ ግጭት በመመልመል መወንጀላቸውን የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ኮሚሽኑ ያዘጋጃቸው የተሃድሶ ማዕከላት፦
በደቡባዊ ዞን ያሉ የቀድሞ ታጣቂዎችና አመራሮች - በማይጨው እና መኾኒ ከተሞች
በደቡብ ምስራቅ ዞን መቐለን ጨምሮ ያሉ - በመቐለ ከተማ በሚገኘው የሰሜን ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ
በምስራቃዊ ዞን ዓዲግራት አካባቢ ያሉ - በዓዲግራት እና ውቅሮ ከተሞች
በማዕከላዊ ዞን አክሱም፣ ዓድዋ፣ ዓብዪዓዲን ጨምሮ የሚገኙ - በዓድዋ፣ አክሱም እና ዓብዪዓዲ ከተሞች
በሰሜን ምዕራብ ዞን ያሉ ታጣቂዎች - ሽረ ከተማ በሚገኘው የቀድሞ ማዕከላዊ እዝ ጠቅላይ መምሪያ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X