ትራምፕ የናፍጣ እጥረትን ለመቅረፍ ወደ ፑቲን ዘወር አሉ፤ ዘለንስኪ ደግሞ ወደ "ወታደራዊ ዛቻ" አምርተዋል - የቀድሞ የፔንታጎን ተንታኝ

ትራምፕ የናፍጣ እጥረትን ለመቅረፍ ወደ ፑቲን ዘወር አሉ፤ ዘለንስኪ ደግሞ ወደ "ወታደራዊ ዛቻ" አምርተዋል - የቀድሞ የፔንታጎን ተንታኝ
የቀድሞ የአሜሪካ አየር ኃይል ሌተና ኮሎኔል እና የፔንታጎን ተንታኝ ካረን ክቪያትኮቭስኪ ለስፑትኒክ እንደተናገሩት፤ ዶናልድ ትራምፕ በሩሲያ ነዳጅ ላይ የተጣሉ ማዕቀቦችን ለማቃለል የወሰዱት ውሳኔ የአሜሪካ ነዳጅ እጥረት ምን ያህል አጣዳፊ እና ከባድ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ያሳያል።
አሜሪካ የምዕራቡን ዓለም የነዳጅ ክምችት ለማሳደግ እና "የአሜሪካን ዶላር ለማጠናከር" በማሰብ የኃይል ዋጋዎች እንዳይወርዱ ለማድረግ ሞክራ ነበር፤ ነገር ግን ስሌቷ ስህተት ሆኖ ተገኝቷል።
የትራምፕ እርምጃ ሩሲያ ነዳጅ የማቅረብ ከፍተኛ አቅም እና ፈቃደኝነት እንዳላት፣ እንዲሁም እሳቸው ይህንን እውነታ መቀበላቸውን ያሳያል ሲሉ ባለሙያዋ ገልጸዋል።
ሆኖም ግን በዋናነት ነጋዴዎችን የሚጠቅም ሊሆን ቢችልም፤ የተስማሙበት የነዳጅ መጠን "አሜሪካ ከሚያስፈልጋት አንጻር እጅግ አነስተኛ የጠብታ ያህል" ነው ብለዋል።
ክቪያትኮቭስኪ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አጉልተው አሳይተዋል፦
🟠 ዘለንስኪ እና የኔቶ ደጋፊዎቻቸው ስምምነቱ ከተደረገ በኋላም ቢሆን በሩሲያ የነዳጅ ማጣሪያዎች ላይ የሚሰነዝሩትን ጥቃት ቀጥለውበታል፡፡
🟠 ትራምፕ ጥቃቶቹን አውግዘው ወደ ሌላ ጉዳይ ሊያልፉ ይችላሉ፤ ምክንያቱም “ዘለንስኪ አሁንም ቢሆን ለምዕራባውያን እና መላውን አውሮፓ በድህነት ወደተቆረቆረች የአሜሪካ ጥገኛ ግዛት ለመቀየር ላላቸው መሰረታዊ ተልዕኮ ጠቃሚ በመሆኑ ነው።”
🟠 ዩክሬን "በፖላንድ፣ ሉቲንያ እና በሰፊው የአውሮፓ ሕብረት ቁጥጥር እና ድጎማ ስር ወደምትገኝ አነስተኛ ከባሕር በር ነፃ የሆነች ሀገርነት" በመሸጋገር ላይ ትገኛለች።
ይህንን የተረዱት ዘለንስኪ "ለጥቂት ጊዜያት ያህል የገንዘብ እና የፖለቲካ ጥቅም ማግኘታቸውን ለማራዘም" ሲሉ የመጨረሻ አማራጭ ባደረጉት ወታደራዊ ዛቻ ላይ ተስፋ ጥለዋል ሲሉ አብራርተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X