ናይጄሪያ በ774 የአካባቢ አስተዳደሮቿ የሕጻናት አመጋገብን ለማሻሻል የኢትዮጵያን ሞዴል ልትተገብር ነው
20:22 10.10.2026 (የተሻሻለ: 20:24 10.10.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ናይጄሪያ በ774 የአካባቢ አስተዳደሮቿ የሕጻናት አመጋገብን ለማሻሻል የኢትዮጵያን ሞዴል ልትተገብር ነው
የናይጄሪያ ፌደራል መንግሥት፣ የክልል አስተዳዳሪዎችና ሚኒስትሮች የኢትዮጵያን የሥነ-ምግብ ፕሮግራም ልምድ በመውሰድ በ774ቱም የናይጄሪያ የወረዳ/የአካባቢ አስተዳደሮች ተግባራዊ የሚያደርጉትን "ኑትሪሽን 774" የተሰኘ ሀገራዊ ፕሮግራም ይፋ አድርገዋል።
በምክትል ፕሬዝዳንት ካሺም ሼቲማ የተመራው የናይጄሪያ ከፍተኛ ልዑክ በኢትዮጵያ ያደረገውን ጉብኝት ተከትሎ፣ ሁለቱ ሀገራት በሕፃናት እድገት መግታት እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት መከላከል ዙሪያ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል የትብብር ፍኖተ-ካርታ ለማዘጋጀት ተስማምተዋል።
ናይጄሪያ ከኢትዮጵያ ተሞክሮ በመውሰድ ከፅንስ እስከ 2 ዓመት ባለው የህፃናት እድሜ (የመጀመሪያዎቹ 1,000 ቀናት) ላይ ያተኮረ የተቀናጀ የጤና፣ ግብርና፣ ትምህርትና የንጹህ ውሃ አቅርቦት ስራዎችን በታችኛው ሕብረተሰብ ደረጃ እንደምታከናውን ሚኒስትሩ ገልፀዋል።
አቡጃ የኢትዮጵያን የጤና ኤክስቴንሽን አሰራር በመከተል፣ በገጠር መንደሮች የሚገኙ ሕጻናትንና ነፍሰ ጡር እናቶችን በቅርበት የመከታተልና የማማከር ስራዎችን ለማጠናከር አቅዳለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X