የቡርኪና ፋሶ ተመራማሪዎች የወባ እና የዴንጌ ትኩሳትን የሚከላከል ተፈጥሯዊ የትንኝ ማጥፊያ አበለፀጉ
18:25 10.10.2026 (የተሻሻለ: 18:34 10.10.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የቡርኪና ፋሶ ተመራማሪዎች የወባ እና የዴንጌ ትኩሳትን የሚከላከል ተፈጥሯዊ የትንኝ ማጥፊያ አበለፀጉ
በቡርኪና ፋሶ የሚገኘው የጆሴፍ ኪ-ዘርቦ ዩኒቨርሲቲ ከካሎትሮፒስ ፕሮሴራ ቅጠሎች የተዘጋጀ እና የወባ እንዲሁም የዴንጊ ትኩሳት አስተላላፊ የሆኑትን የአኖፌሊስ ጋምቢያ እና የኤደስ ኤጅፕቲ ትንኞች ትል የሚያጠፋ ምርት አዘጋጅቷል።
የፕሮጀክቱ ምርምር ውጤት በመስከረም 28 ይፋ የተደረገ ሲሆን የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች ይዟል፦
▪ የተደረጉት ፍተሻዎች እና ሙከራዎች ምርቱ የትንኝ ትሎችን የማጥፋት አቅሙ ከ80 እስከ 90 በመቶ መሆኑን አሳይተዋል፡፡
▪ ምርቱ የመግደል አቅሙ ለረጅም ጊዜ እንዲቆይ ታስቦ በታብሌት መልክ የተዘጋጀ ነው፡፡
▪ ፕሮጀክቱ ወደ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ ገደማ የሚጠጋ ጊዜ ፈጅቷል፡፡
▪ የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ ሀገር በቀል የመፍትሔ አማራጭ ማቅረብ እና በኬሚካል ፀረ-ተባዮች ላይ ያለውን ጥገኝነት መቀነስ ነው።
ተመራማሪዎቹ በቀጣይም ሙከራዎቻቸውን በመቀጠል ይህንን ተፈጥሯዊ የትንኝ ማጥፊያ በአነስተኛ ወጪ እና በሰፊው የማምረት ሥራ ላይ ለማተኮር ይፈልጋሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X