ኢትዮጵያ እና ፓኪስታን በትምህርትና ቴክኒክ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ አዘጋጁ

© telegram sputnik_ethiopiaኢትዮጵያ እና ፓኪስታን በትምህርትና ቴክኒክ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ አዘጋጁ
ኢትዮጵያ እና ፓኪስታን በትምህርትና ቴክኒክ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ አዘጋጁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.10.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ እና ፓኪስታን በትምህርትና ቴክኒክ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ አዘጋጁ

 

በፓኪስታን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ዑመር ሁሴን ከፓኪስታን የፌደራል ትምህርትና ሙያ ሥልጠና ሚኒስትር ካሊድ ማቅቡል ሲዲቂ ጋር ውይይት አድርገዋል።

 

በውይይቱ ወቅት ሁለቱ ሀገራት በሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ላይ በጋራ ለመስራት መክረዋል፦

 

🟠 የሁለቱ ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎችና የምርምር ተቋማት በቀጥታ እንዲገናኙና የጋራ ሴሚናሮችን እንዲያዘጋጁ፤ የተማሪዎች እና የመምህራን ልውውጥ እንዲደረግ፤

 

🟠 የፓኪስታን ብሔራዊ የሙያና ቴክኒክ ሥልጠና ኮሚሽን ከኢትዮጵያ አቻ ተቋማት ጋር በመሆን በሙያ ብቃት፣ ሥልጠናዎች እና በክህሎት ልውውጥ ላይ በጋራ እንዲሰሩ፤

 

🟠 በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና፣ ሥነ-ጥበብ እና ሂሳብ ትምህርት ዘርፍ የምርምር እና የትምህርት ግብዓቶችን በጋራ ለመጠቀም ሁለቱም ወገኖች ዝግጁነታቸውን ገልጸዋል።

 

ውይይቱ እ.ኤ.አ. በታህሳስ 2025 በዲፕሎማሲያዊ መስመር የቀረበውን የትምህርት ትብብር የመግባቢያ ስምምነት አጠናቆ በፍጥነት ወደ ትግበራ ማሸጋገር ላይ ያተኮረ ነው።

 

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0