https://amh.sputniknews.africa/20261010/5521703.html
ሩሲያ በዓለም አቀፍ የፓርላማዎች ሕብረት ውስጥ የብሪክስ+ ቡድን እንዲቋቋም ሐሳብ አቀረበች - የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ
ሩሲያ በዓለም አቀፍ የፓርላማዎች ሕብረት ውስጥ የብሪክስ+ ቡድን እንዲቋቋም ሐሳብ አቀረበች - የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ
Sputnik አፍሪካ
ሩሲያ በዓለም አቀፍ የፓርላማዎች ሕብረት ውስጥ የብሪክስ+ ቡድን እንዲቋቋም ሐሳብ አቀረበች - የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ"የብሪክስ+ ቡድን ሐሳብ ዓላማው [በሕብረቱ ውስጥ ባሉ] አምስት እና ምናልባትም በስድስቱም ጂኦፖለቲካዊ ቡድኖች... 10.10.2026, Sputnik አፍሪካ
2026-10-10T16:59+0300
2026-10-10T16:59+0300
2026-10-10T17:04+0300
sputnik africa
telegram sputnik_ethiopia
https://cdn.amh.sputniknews.africa/img/07ea/0a/0a/5521550_94:0:1186:614_1920x0_80_0_0_05ea410949b32a3ae1d2159db37ac368.jpg
ሩሲያ በዓለም አቀፍ የፓርላማዎች ሕብረት ውስጥ የብሪክስ+ ቡድን እንዲቋቋም ሐሳብ አቀረበች - የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ"የብሪክስ+ ቡድን ሐሳብ ዓላማው [በሕብረቱ ውስጥ ባሉ] አምስት እና ምናልባትም በስድስቱም ጂኦፖለቲካዊ ቡድኖች መካከል የተሻለ መግባባትና ትብብር የሚፈጥር፣ እርስ በርሳቸው የሚደጋገፉበት እንዲሁም የራሳቸውን ፍላጎት በሌሎች ላይ ከመጫን ይልቅ ፍላጎቶቻቸውን በጋራ የሚያስፈጽሙበት የመድረክ ምህዳር መፍጠር ነው" ሲሉ ኮንስታንቲን ኮሳቼቭ ለመገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ የፓርላማዎች ሕብረት ውስጥ ስድስት ጂኦፖለቲካዊ ቡድኖች ይገኛሉ፤ ከእነዚህ ውስጥ አምስቱ ከፖለቲካ ነፃ ሆነው በጂኦግራፊያዊ ቀጣናዎች የተደራጁ ናቸው። ነገር ግን የምዕራባውያኑ ቡድን (ቡድን 12+) በራሱ አምባገነናዊ ርዕዮተ-ዓለም የተደራጀ፣ ጥብቅ ዲሲፕሊን ያለው እና አብላጫ ድምፅ ባይኖረውም እንኳ የራሱን ፖለቲካዊ አጀንዳ እና ፍላጎት በሌሎች አባላት ላይ የሚጭን ነው ሲሉ ኮሳቼቭ ገልጸዋል። በሩሲያ የቀረበው አዲሱ የብሪክስ+ ቡድን ከማንኛውም ገዥ ርዕዮተ-ዓለም ነፃ የሆነ፣ ነገር ግን በሥራው ላይ እጅግ ውጤታማ የሆነ ሕብረት እንደሚሆን አብራርተዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
2026
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
https://cdn.amh.sputniknews.africa/img/07ea/0a/0a/5521550_231:0:1050:614_1920x0_80_0_0_4262afa518cef41df0dab7f707381a7b.jpgSputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
ሩሲያ በዓለም አቀፍ የፓርላማዎች ሕብረት ውስጥ የብሪክስ+ ቡድን እንዲቋቋም ሐሳብ አቀረበች - የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ
16:59 10.10.2026 (የተሻሻለ: 17:04 10.10.2026) ሩሲያ በዓለም አቀፍ የፓርላማዎች ሕብረት ውስጥ የብሪክስ+ ቡድን እንዲቋቋም ሐሳብ አቀረበች - የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ
"የብሪክስ+ ቡድን ሐሳብ ዓላማው [በሕብረቱ ውስጥ ባሉ] አምስት እና ምናልባትም በስድስቱም ጂኦፖለቲካዊ ቡድኖች መካከል የተሻለ መግባባትና ትብብር የሚፈጥር፣ እርስ በርሳቸው የሚደጋገፉበት እንዲሁም የራሳቸውን ፍላጎት በሌሎች ላይ ከመጫን ይልቅ ፍላጎቶቻቸውን በጋራ የሚያስፈጽሙበት የመድረክ ምህዳር መፍጠር ነው" ሲሉ ኮንስታንቲን ኮሳቼቭ ለመገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ የፓርላማዎች ሕብረት ውስጥ ስድስት ጂኦፖለቲካዊ ቡድኖች ይገኛሉ፤ ከእነዚህ ውስጥ አምስቱ ከፖለቲካ ነፃ ሆነው በጂኦግራፊያዊ ቀጣናዎች የተደራጁ ናቸው። ነገር ግን የምዕራባውያኑ ቡድን (ቡድን 12+) በራሱ አምባገነናዊ ርዕዮተ-ዓለም የተደራጀ፣ ጥብቅ ዲሲፕሊን ያለው እና አብላጫ ድምፅ ባይኖረውም እንኳ የራሱን ፖለቲካዊ አጀንዳ እና ፍላጎት በሌሎች አባላት ላይ የሚጭን ነው ሲሉ ኮሳቼቭ ገልጸዋል።
በሩሲያ የቀረበው አዲሱ የብሪክስ+ ቡድን ከማንኛውም ገዥ ርዕዮተ-ዓለም ነፃ የሆነ፣ ነገር ግን በሥራው ላይ እጅግ ውጤታማ የሆነ ሕብረት እንደሚሆን አብራርተዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X