ናይጄሪያ የምግብ ዋስትናዋን ለማረጋገጥ የኢትዮጵያን የዘመናዊ ግብርና ሞዴል ልትከተል ነው

© telegram sputnik_ethiopiaናይጄሪያ የምግብ ዋስትናዋን ለማረጋገጥ የኢትዮጵያን የዘመናዊ ግብርና ሞዴል ልትከተል ነው
ናይጄሪያ የምግብ ዋስትናዋን ለማረጋገጥ የኢትዮጵያን የዘመናዊ ግብርና ሞዴል ልትከተል ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.10.2026
ሰብስክራይብ

ናይጄሪያ የምግብ ዋስትናዋን ለማረጋገጥ የኢትዮጵያን የዘመናዊ ግብርና ሞዴል ልትከተል ነው

 

የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት ካሺም ሼቲማ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የመስኖ፣ ስንዴና የግብርና ልማት ከጎበኙ በኋላ፣ ናይጄሪያ የግብርና ምርታማነቷን ለማሳደግና ጥገኝነትን ለማስቀረት የኢትዮጵያን የዘመናዊ ግብርና ስኬት ልምድ ለመተግበር ማቀዷን አስታውቀዋል።

 

ምክትል ፕሬዝዳንቱ የኢትዮጵያና ናይጄሪያ የመሪዎች ልምድ ልውውጥ መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ "በምግብ ራስን አለመቻል የሀገርን ሉዓላዊነት ያጎድላል፤ ኢትዮጵያ ለቀጣናው አብነት የሚሆን ታላቅ ስኬት አስመዝግባለች" ብለዋል።

 

ምክትል ፕሬዝዳንቱ ስለ ኢትዮጵያ ስኬት የገለጿቸው ቁልፍ መግለጫዎች፦

 

በዓመት እስከ 1 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ይደረግበት የነበረው የስንዴ ገቢ በሀገር ውስጥ ምርት ሙሉ በሙሉ ተተክቷል።

 

አሁን ላይ ከ3.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ በማመንጨት ለጎረቤት ሀገራት መላክ ተጀምሯል።

 

ናይጄሪያ ከኢትዮጵያ የተሻሻሉ ዝርያዎች አጠቃቀም፣ በዘመናዊ የግብርና መሳሪያዎች መታገዝ እና የአየር ንብረት ተስማሚ አሰራሮችን በመውሰድ የሀገር ውስጥ የስንዴ ምርቷን ማሳደግ እንደምትፈልግ ጠቁመዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0