የሊቢያው የሱቡል አል-ሰላም ብርጌድ በኩፍራ ከተደረገ የተኩስ ልውውጥ በኋላ 1.3 ሚሊዮን አደንዛዥ ዕፆችን በቁጥጥር አዋለ

ሰብስክራይብ

የሊቢያው የሱቡል አል-ሰላም ብርጌድ በኩፍራ ከተደረገ የተኩስ ልውውጥ በኋላ 1.3 ሚሊዮን አደንዛዥ ዕፆችን በቁጥጥር አዋለ

ከመከላከያ መግለጫው ጋር የተሰራጩ ፎቶዎች እንደሚያሳዩት፤ ወታደሮቹ '1' የሚል ቁጥር እና በግልፅ ጥቁር ፅሁፍ 'በጀርመን የተሰራ' የሚል ምልክት ያረፈባቸውን ነጫጭ ድቡልቡል እንክብሎች የያዙ በደርዘን የሚቆጠሩ ግልጽ የፕላስቲክ ከረጢቶችን ከበው ይታያሉ።

ብርጌዱ የምድር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ አካል ሲሆን በምስራቅ ሊቢያ ለሚገኘው የሊቢያ ብሔራዊ ጦር ወታደራዊ አዛዥ ካሊፋ ሀፍታር ተጠሪ ነው።

የተባበሩት መንግሥታት የዕፅ እና ወንጀል ጽሕፈት ቤት የጥር ሪፖርት እንደሚያመለክተው፤ ሊቢያ ለሀገር ውስጥ ተጠቃሚዎች እና በመላው የአፍሪካ አኅጉር ለሚገኙ ገበያዎች የሚላኩ ሰው ሠራሽ ዕፆች እና ሌሎች አደንዛዥ ዕፆች የሚሸጋገሩባት ዋነኛ ቀጣናዊ የማስተላለፊያ ማዕከል ሆናለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0