የሕንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የደቡብ ዓለም ሀገራት ቀውሶችን በጋራ እንዲመክቱ ጥሪ አቀረቡ
15:35 10.10.2026 (የተሻሻለ: 15:44 10.10.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሕንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የደቡብ ዓለም ሀገራት ቀውሶችን በጋራ እንዲመክቱ ጥሪ አቀረቡ
ሚኒስትሩ ሱብራህማንያም ጃይሻንካር፣ በደቡባዊ ዓለም ሀገራት ላይ የተደቀኑትን የነዳጅ፣ የምግብ፣ የማዳበሪያ እና የፋይናንስ ቀውሶች በጋራ ለመመከት የላቀ ትብብርና ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ በትናንትናው ዕለት በአድዋ ድል መታሰቢያ ባደረጉት ሕዝባዊ ገለጻ ላይ ማሳሰባቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጥሪ ዋና ዋና ነጥቦች፦
🟠 የደቡባዊ ዓለም ሀገራት ከኮቪድ-19 ወረርሽኝም ሆነ ከአሁን ግጭቶች ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት (አስተዋጽኦ) ባይኖራቸውም፣ የችግሮቹ ዋና ገፈት ቀማሾች በመሆን እድገታቸው ተጓቷል።
🟠 በነዳጅ፣ በምግብ፣ በማዳበሪያ እና በፋይናንስ ረገድ የተፈጠሩትን አጣዳፊ ቀውሶች በጋራ መመከት ያስፈልጋል።
🟠 ለችግሮቹ መፍትሄ ለመፈለግ “የላቀ ፖለቲካዊ ቁርጠኝነትና ውሳኔ ያስፈልጋል፡፡”
🟠 ትብብሩ ሌሎችን ያገለለ ወይም በሌሎች ሀገራት ላይ ያተኮረ ሊሆን አይገባም።
🟠 የደቡባዊ ዓለም ሀገራት ያላቸውን ሀብት፣ ልምድና ብቃት በማቀናጀት የጋራ አቅማቸውን መገንባት አለባቸው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X