ኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣውን የሳይበር ስጋት ለመመከት 7ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ይፋ አደረገች

© telegram sputnik_ethiopiaኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣውን የሳይበር ስጋት ለመመከት 7ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ይፋ አደረገች
ኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣውን የሳይበር ስጋት ለመመከት 7ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ይፋ አደረገች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.10.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣውን የሳይበር ስጋት ለመመከት 7ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ይፋ አደረገች

 

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ያስጀመረው እና ከጥቅምት 1 እስከ 30 ቀን 2019 ዓ.ም የሚቆየው ይህ የሳይበር ደህንነት ወር በዜጎች፣ በተቋማትና ቁልፍ መሠረተ ልማቶች ላይ የሚቃጣውን የሳይበር ጥቃት ለመመከትና የኅብረተሰቡን ንቃተ-ህሊና ለማጎልበት ያለመ ነው።

የወሩ ዋና ዋና ትኩረቶች፦

 

የሕፃናት የበይነ-መረብ ጥብቃ፣

ሰው ሠራሽ አስተውሎት፣

ዲጂታል 2030 እና የቁልፍ መሠረተ ልማቶች ዝግጁነት።

 

የታቀዱ መርሃ-ግብሮች፦

 

የታዳጊዎችና ወጣቶች የ”ካች ዘ ፍላግ” ውድድር

በትምህርት ተቋማት የሳይበር ክበባት እንቅስቃሴዎች

የዲጂታል ንቅናቄዎች እና

የማኅበራዊ ሚዲያ የአጭር ፊልም ውድድሮች

 

በኢትዮጵያ በ2018 በጀት ዓመት ብቻ ከ71 ሺህ በላይ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች መመዝገባቸውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ ጠቅሰዋል።

 

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0