ሩሲያ በዩክሬን ያሏት ዓላማዎች አልተቀየሩም ሲሉ ፑቲን ለትራምፕ ገለጹ - ክሬምሊን
10:25 10.10.2026 (የተሻሻለ: 10:34 10.10.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያ በዩክሬን ያሏት ዓላማዎች አልተቀየሩም ሲሉ ፑቲን ለትራምፕ ገለጹ - ክሬምሊን
እንደ ፕሬዝዳንታዊ ረዳቱ ዩሪ ኡሻኮቭ ገለጻ፤ ዩክሬን ምርጫዎችን ለማስተጓጎል በመሞከሯ እና በሲቪሎች ላይ ጥቃት በመሰንዘሯ አፋጣኝ ድርድሮች የሚደረጉበትን ዕድል ዘግታዋለች ሲሉ ቭላድሚር ፑቲን ለትራምፕ ተናግረዋል።
ኡሻኮቭ መስከረም 29 በፑቲን እና ትራምፕ መካከል የተደረገውን የስልክ ውይይት ዝርዝር ነጥቦች አብራርተዋል፦
▫ ዩክሬን የሩሲያን ግስጋሴ ለማስቆም የምታደርገው ሙከራ "ምንም ዓይነት ተስፋ የለውም"፤ የሩሲያ ጦር ሙሉ በሙሉ የመቀዳደም እድሉን በእጁ በማድረግ ወደፊት እየገሰገሰ ይገኛል፡፡
▫ ትራምፕ ለፑቲን የልደት መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል። መስከረም 27 ዊትኮፍ ለኡሻኮቭ ደውለው ትራምፕ ከፑቲን ጋር በአካል ለመነጋገር እንደሚፈልጉ እና በቅርቡም እንደሚገናኙ ተስፋ እንደሚያደርጉ ገልጸው ነበር፡፡
▫ ዲፕሎማሲያዊ ዕድሎች አሁንም ስላላበቁ አሜሪካ እና ኢራን በድርድር ላይ እንዲቀመጡ የማድረጉ አስፈላጊነት ላይ ፑቲን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
▫ በፑቲን እና ትራምፕ መካከል የሚደረግ ስብሰባ እስካሁን በዝርዝር አልተመካከሩበትም። እንደ ኡሻኮቭ ገለጻ ሁለቱም በእስያ-ፓሲፊክ የኢኮኖሚ ትብብር ጉባኤ ላይ ከተገኙ ሊገናኙ ይችላሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X