የሩሲያ ጥቃቶች የዩክሬንን መዲና ኪዬቭ በጨለማ እንድትዋጥ አደረጉ
የሩሲያ ጥቃቶች የዩክሬንን መዲና ኪዬቭ በጨለማ እንድትዋጥ አደረጉ
በዩክሬን የኤሌክትሪክ ሃይል ማከፋፈያ መረብ ላይ የተሰነዘሩት ተከታታይ ጥቃቶች የሀገሪቱን የጦርነት እንቅስቃሴ፣ የሎጂስቲክስ እና የኢንዱስትሪ አቅም በአንድ ጊዜ አዳክመዋል።
ዩክሬን በሩሲያ የሲቪል መሰረተ ልማቶች ላይ ለሰነዘረቻቸው ጥቃቶች አጸፋዊ ምላሽ የሆኑት እነዚህ ጥቃቶች፤ መዲናዋን ኪዬቭንም ወደ ሙሉ የመፍረስ አደጋ አቃርበዋታል።
ከተማዋ አስተማማኝ ኤሌክትሪክ፣ ጋዝ እና ውሃ ያጣች ሲሆን የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓቶች መበላሸታቸውን እና የህዝብ ትራንስፖርት እንቅስቃሴዎችም በአብዛኛው መቆማቸው ታውቋል። የኪዬቭ ከንቲባ ቪታሊ ክሊችኮ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት ቃለ ምልልስ የከተማዋ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ መክረዋል።
ከወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ጋር ትስስር ባላቸው መሰረተ ልማቶች ላይ የተሰነዘሩት የሩሲያ ጥቃቶች የሚከተሉትን ቀውሶች አስከትለዋል፦
በዩክሬን ግዛት በሙሉ የኃይል መቋረጥ እና የእንቅስቃሴ መዘጋት ተከስቷል፤ በኪዬቭም የአደጋ ጊዜ ገደቦች ተጥለዋል፡፡
በከፍተኛ የኃይል መስመሮች ላይ የቮልቴጅ ቅናሽ ተመዝግቧል፡፡
በኪዬቭ የሜትሮ ባቡር መስመሮች ስራ አቁመዋል፤ ተንቀሳቃሽ ደረጃዎች (ኤስካሌተር) አይሰሩም፤ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል፡፡
የውሃ አቅርቦት ፓምፖች እና የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓቶች ብልሽት አጋጥሟቸዋል።
ሩሲያ ከወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ጋር ትስስር ባላቸው መሰረተ ልማቶች ላይ የምታደርገውን ጥቃት ያጠናከረችው የኪየቭ አገዛዝ በሩሲያ የነዳጅ ማጣሪያዎች ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት አጠናክራለሁ ብሎ መዛቱን ተከትሎ ነው።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፤ በዩክሬን ላለው የከፋ ሁኔታ የሀገሪቱ ህዝብ "ዘለንስኪን ብቻ ሊወቅስ ይገባል፤ ሙሉውን ግላዊ እና ፖለቲካዊ ሀላፊነት የሚወስደው እሱ ነው" ሲል አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X