የአፍሪካ የብድር ደረጃ ምዘና ተቋም ማቋቋሙ በጣም ስልታዊ እርምጃ ነው – ባለሙያ

ሰብስክራይብ

የአፍሪካ የብድር ደረጃ ምዘና ተቋም ማቋቋሙ በጣም ስልታዊ እርምጃ ነው – ባለሙያ

 

የአፍሪካ ሕብረት ይፋ ያደረገው ተቋም ምንም እንኳን እጅግ ዘግይቶ የመጣ ቢሆንም መከናወኑ ሊያስደስተን ይገባል ሲሉ የኢኮኖሚ ባለሙያ፣ የቢዝነስ ሰው እና ፖለቲከኛ አማንይሁን ረዳ የተቋሙን ምሥረታ አስመልክቶ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ ገልጸዋል፡፡

 

“አብዛኞቹ አፍሪካውያን ተበዳሪዎች ከፍተኛ ስጋት ያለባቸው ተበዳሪዎች ተደርገው ይፈረጃሉ። ይህን የሚያደርጉትም የብድር ደረጃ ምዘና ተቋማት በአፍሪካ እቅም ላይ ከፍተኛ የርዕዮተ ዓለም አድሏዊነት ስላለባቸው ነው። ስለዚህ የራሳችን የብድር ምዘና ተቋም መኖሩ ከእነዚህ ችግሮች የተወሰኑትን ይፈታል።”

 

ዓለም አቀፍ የደረጃ ምዘናተቋማት የአኅጉሪቱ ሀገራት ላይ ሊኖሩ የሚችሉ ስጋቶችን መጠን በማጋነን፣ የአፍሪካ የኢኮኖሚ ተግዳሮቶችን የመቋቋም አቅም ዝቅ አድርገው እንደሚገምቱም አማንይሁን ረዳ  ጠቁመዋል።

 

“በሌላው ዓለም እንዳለው ሁሉ በአፍሪካም ውስጥ ስጋቶች አሉ፤ ስጋቶቹ በተገቢው መልኩ ሊመዘኑ ይገባል። በጣም ሊጋነኑ አይገባም፤ ዕዳችንን የመክፈል አቅማችንም ቢሆን ከግምት ውስጥ ሊገባ ይገባል። የአፍሪካ ሀገራት ዕዳቸውን በጊዜው እና በአግባቡ ከሚከፍሉ በጣም ታማኝ ሀገራት መካከል ይጠቀሳሉ።”

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0