የሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአፍሪካ እና ሕንድ አጋርነት ላይ ያተኮረ ሕዝባዊ ገለጻ እያደረጉ ነው
16:10 09.10.2026 (የተሻሻለ: 17:04 09.10.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአፍሪካ እና ሕንድ አጋርነት ላይ ያተኮረ ሕዝባዊ ገለጻ እያደረጉ ነው
ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ የሚገኙት ሱብራህማንያም ጃይሻንካር፣ በሕንድ እና በአፍሪካ መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት፣ በአድዋ ድል መታሰቢያ የከፍተኛ ደረጃ ሕዝባዊ ገለጻ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል።
ገልጻቸው የደቡብ-ደቡብ ትብብር እና የወደፊት የጋራ እድገት ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ታውቋል፡፡
ቀደም ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከኢትዮጵያው አቻቸው ጌዲዎን ጢሞቲዎስ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳይ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መንግሥት ሙዚየምን የጎበኙት ጃይሻንካር፣ ቦታው የኢትዮጵያን የበለፀገ ባህል፣ ቅርሶች እና ጥልቅ ታሪክ በግልጽ እንደሚያሳይ በማኅበራዊ ሚዲያ ገልጸዋል።
ጃይሻንካር በአዲስ አበባ ቆይታቸው በአፍሪካ የሚገኙ የሕንድ የዲፕሎማቲክ መሪዎችን ስብሰባ በሊቀመንበርነት እንደሚመሩ ተገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X