"ለአዳዲስ ትስስሮች ክፍት ነን" - የሞስኮ የወጪ ንግድ ማዕከል
15:45 09.10.2026 (የተሻሻለ: 15:54 09.10.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
"ለአዳዲስ ትስስሮች ክፍት ነን" - የሞስኮ የወጪ ንግድ ማዕከል
የሞስኮ የወጪ ንግድ ማዕከል በሕክምና እና በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፎች የተሰማሩ 15 ኩባንያዎችን ያቀፈ የንግድ ልዑክ ወደ ደቡብ አፍሪካ በመላክ በጆሃንስበርግ በተካሄደው 'የዓለም ጤና ኤክስፖ' ኤግዚቢሽን ላይ ምርቶቻቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ ማስተዋወቃቸውን የማዕከሉ የዓለም አቀፍ ሁነቶች ክፍል ኃላፊ ማርያም ጋሳኖቫ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።
"የእኛን የሞስኮ ኩባንያዎች ፍላጎት መሠረት በማድረግ ተስማሚ አጋሮችን እየፈለግንላቸው እንገኛለን። በውጭ ሀገራት ገበያ ያላቸውን ልምድ እና በደቡብ አፍሪካ ምን መስራት እንደሚፈልጉም እየጠየቅን እናስተባብራለን" ሲሉ ጋሳኖቫ ተናግረዋል።
ማዕከሉ ምርቶቻቸውን ወደ ውጭ ሀገር የሚልኩ ከ4,000 በላይ ኩባንያዎችን ይደግፋል። የአሁኑ ልዑክ በህክምና እና በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ላይ ያተኮረ ቢሆንም የወደፊት ልዑካን ሌሎች ዘርፎችን ወደ አህጉሪቱ ሊያመጡ ይችላሉ።
ቀደም ሲል 'አፍሪካ ኧልዝ' በመባል ይታወቅ የነበረው የጆሃንስበርጉ የዓለም የጤና ኤግዚቢሽን ከመስከረም 26 እስከ 28 ተካሂዷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X