የሰው ሠራሽ አስተውሎት ልማት እና ዲጂታል ኢኮኖሚ በሩሲያ እና አፍሪካ ግንኙነት ውስጥ ቀዳሚ ትኩረት ተሰጥቷቸዋል - የሩሲያ ስቴት ዱማ ምክትል አፈ-ጉባኤ
14:18 09.10.2026 (የተሻሻለ: 14:24 09.10.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሰው ሠራሽ አስተውሎት ልማት እና ዲጂታል ኢኮኖሚ በሩሲያ እና አፍሪካ ግንኙነት ውስጥ ቀዳሚ ትኩረት ተሰጥቷቸዋል - የሩሲያ ስቴት ዱማ ምክትል አፈ-ጉባኤ
ሌሎች ቀዳሚ ትኩረት የተሰጣቸው ዘርፎች በሀገር ውስጥ ገንዘቦች የሚፈጸሙ ክፍያዎችን፣ የምግብ እና የሰው ሠራሽ ማዳበሪያ አቅርቦቶችን፣ በአካደሚክ ዘርፍ ለአፍሪካውያን የሚሰጡ ስልጠናዎችን እንዲሁም የኒውክሌር ኃይል ትብብርን እንደሚያካትቱ ቪክቶሪያ አብራምቼንኮ ለሩሲያ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።
"አፍሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ተፅዕኖ ፈጣሪ አኅጉር ናት፤ የሩሲያ ዲፕሎማሲም ከአኅጉሪቱ ጋር የረጅም ጊዜ ስልታዊ ቁርጠኝነት አለው" ሲሉ አብራምቼንኮ ገልጸዋል።
የኒውክሌር ኃይል እንደ ዋና ማሳያ፦ የሩሲያ ፓርላማ አባሏ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አብራርተዋል፦
በግብፅ በሩሲያ ንድፍ እየተገነባ በሚገኘው የኤል ዳባ የኒውክሌር ጣቢያ አራት ክፍሎች በአንድ ጊዜ በመገንባት ላይ ይገኛሉ፤
ከአያሌ የአፍሪካ ሀገራት ጋር አነስተኛ የኑክሌር ኃይል ማመንጫዎች ስምምነቶች ተፈረመዋል፤
ለዘርፉ የሚያስፈልጉ የባለሙያዎች ስልጠናም በስፋት እየተሰጠ ይገኛል።
ፍላጎቱ የሁለቱም ወገን ነው፦ ከ54ቱ የአፍሪካ ሀገራት መካከል ከ30 በላይ የሚሆኑት ከጥቅምት 18 እስከ 20 በሞስኮ በሚካሄደው ሦስተኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አሁኑኑ ያረጋገጡ መሆናቸው ተገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X