አንዲት ኒጀራዊት እናት በአራት ደቂቃ ውስጥ አምስት መንትያ ልጆችን ወለደች
10:00 09.10.2026 (የተሻሻለ: 10:04 09.10.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
አንዲት ኒጀራዊት እናት በአራት ደቂቃ ውስጥ አምስት መንትያ ልጆችን ወለደች
የመጀመሪያዋ ሴት ልጅ ከጠዋቱ 4:43 ላይ የተወለደች ሲሆን አምስተኛዋ ደግሞ በ4:47 ላይ መወለዷን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ልጅ ለማግኘት ለረጅም ጊዜ ስትመኝ የነበረችው እናት የፅንስ ማበልጸጊያ ሕክምና ስትከታተል ቆይታለች። በስምንት ወራቸው የተወለዱት አምስቱ ህፃናት እና እናታቸው በአሁኑ ወቅት በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛሉ። ህፃናቱ በአሁኑ ጊዜ በጨቅላ ህፃናት ሕክምና ክፍል ውስጥ ክትትል እየተደረገላቸው የሚገኝ ሲሆን፥ ምንም ዓይነት የኦክስጅን ድጋፍ አላስፈለጋቸውም ተብሏል።
አጠቃላይ የሕክምና ባለሙያ የሆኑት ዶክተር ፓስካሊን ካክፖ ቺ ቺ እንደገለጹት፤ እናቲቱ አምስት መንትያ ልጆችን እንደሚወልዱ ከተነገራቸው ወራት ተቆጥረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X