ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ አስቸኳይ የግብርና ኢንቨስትመንት ያስፈልጋቸዋል - ፋኦ
19:15 08.10.2026 (የተሻሻለ: 19:24 08.10.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ አስቸኳይ የግብርና ኢንቨስትመንት ያስፈልጋቸዋል - ፋኦ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብ እና እርሻ ድርጅት ልዑክ በቅርቡ በሊባኖስ ያደረገውን ጉብኝት ተከተሎ ባወጣው መግለጫ፤ ግጭቶች፣ ከፍተኛ የሕዝብ መፈናቀል እና ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተያያዙ ቀውሶች የነዋሪዎችን ህይወት እና የዕለት ተዕለት ኑሮ ለአደጋ እያጋለጡት መሆኑን አስታውቋል።
የፋኦ አኃዛዊ መረጃዎች፦
በመካከለኛው ምስራቅ እና በሰሜን አፍሪካ ከ45 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለከፍተኛ የምግብ እጥረት እና ቀውስ ተዳርገዋል።
በሱዳን ብቻ (የአኅጉሪቱ የቀውስ ድርሻ እኩሌታ ያህሉ) 19.5 ሚሊዮን ሰዎች ለከባድ የምግብ ዋስትና እጦት ተጋልጠዋል።
የፋኦ የመፍትሔ ሃሳቦች፦
አርሶ አደሮች የምግብ ምርታቸውን እንዲቀጥሉ እና የቀጣናው የምግብ ዋስትና እጦት እንዳይባባስ ለዘር፣ ለእንስሳት መኖ፣ ለእንስሳት ሕክምና አገልግሎት እና መስኖ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ።
የሰብዓዊ እርዳታ ጥረቶች ከምግብ እርዳታ ባሻገር ማኅበረሰቡ እራሱ ምግብ የማምረት አቅሙን ጠብቆ እንዲቆይ የሚያስችሉ እንዲሆኑ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X