የጎንደር ዩኒቨርስቲ የመምህራን ትምህርት ኮሌጅ የዩኔስኮን ሽልማት አሸነፈ

© telegram sputnik_ethiopiaየጎንደር ዩኒቨርስቲ የመምህራን ትምህርት ኮሌጅ የዩኔስኮን ሽልማት አሸነፈ
የጎንደር ዩኒቨርስቲ የመምህራን ትምህርት ኮሌጅ የዩኔስኮን ሽልማት አሸነፈ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.10.2026
ሰብስክራይብ

የጎንደር ዩኒቨርስቲ የመምህራን ትምህርት ኮሌጅ የዩኔስኮን ሽልማት አሸነፈ

የጎንደር ዩኒቨርስቲ የመምህራን ትምህርትና ባህሪ ሳይንስ ኮሌጅ በመምህራን ሙያ ማበልጸግና በትምህርት ጥራት ማረጋገጥ ዘርፍ ባከናወናቸው ከፍተኛ ተግባራት የ2026 የዩኔስኮ-ሃምዳን ዓለም አቀፍ ሽልማት አሸናፊ ሆኗል።

ኮሌጁ ከ124 የዓለም ሀገራት ከተውጣጡ ተቋማት ጋር ተወዳድሮ 1ኛ በመውጣት የ100 ሺህ ዶላር ተሸላሚ መሆኑ ተገልጿል።

በፈረንሳይ ፓሪስ በተካሄደው የዓለም አቀፍ የመምህራን ቀን ሥነ-ሥርዓት ኮሌጁ በትምህርት መርጃ መሳሪያዎች ምርትና በትምህርት ጥራት ላበረከተው የጎላ አስተዋጽኦ ዕውቅናውን እንዳገኘ አሐዱ ዘግቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0