ናይጄሪያ እና ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ለልጆቿ የሚመጥን አርአያ የመሆን ኃላፊነት አለባቸው - የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት

ሰብስክራይብ

ናይጄሪያ እና ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ለልጆቿ የሚመጥን አርአያ የመሆን ኃላፊነት አለባቸው - የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት

ረቡዕ "በሥርዓተ ምግብ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት" በሚል መሪ ቃል ተዘጋጅቶ በነበረው የኢትዮ-ናይጄሪያ የሥራ አመራር የልምድ ልውውጥ መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት ካሺም ሼቲማ፤ ኢትዮጵያ የሕፃናት መቀንጨርን ለመከላከል እያከናወነች ያለውን ሥራ አድንቀዋል።

“ኢትዮጵያ በሰቆጣ ቃል ኪዳን አማካኝነት በ2030 ዕድሜያቸው ከሁለት ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትን ከመቀንጨር ለመታደግ ያስቀመጠችው ራዕይ አስደናቂ ነው” ብለዋል።

ናይጄሪያ እና ኢትዮጵያ የአፍሪካን ግዙፍ እምቅ አቅም አሟጦ ለመጠቀም የሚያስፈልገውን የመሪነት ሚና መጫወት እንዳለባቸውም አጽንኦት ሰጥተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በበኩላቸው፤ በሰቆጣ ቃል ኪዳን ስር የሕፃናት መቀንጨር እየቀነሰ መምጣቱን ጠቅሰዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0