ሩሲያ የዓለም አቀፉን የወንጀል ፍርድ ቤት ዳኞች ንፁሃንን በማሳደድ ከሳ፤ ተላልፈው እንዲሰጧት ጠየቀች
15:45 08.10.2026 (የተሻሻለ: 15:54 08.10.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያ የዓለም አቀፉን የወንጀል ፍርድ ቤት ዳኞች ንፁሃንን በማሳደድ ከሳ፤ ተላልፈው እንዲሰጧት ጠየቀች
የሩሲያ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ቢሮ ዘጠኝ የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት አባላት ተላልፈው እንዲሰጡት ለኔዘርላንድስ እና ለሌሎች በርካታ ሀገራት ጥያቄ መላኩን አስታውቋል።
እ.ኤ.አ ታህሳስ 2025 የሞስኮ ፍርድ ቤት "ንጹሃንን በመክሰስ፣ ሕገ-ወጥ እስራት በመፈጸም እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥበቃ የሚደረግላቸውን ግለሰቦች በማጥቃት" ወንጀል በሌሉበት እስከ 15 ዓመት በሚደርስ እስራት ቀጥቷቸዋል። የፍርድ ቤቱን ዋና ዐቃቤ ሕግ እና ፕሬዝዳንት ጨምሮ ሁሉም ግለሰቦች አሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፈላጊ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተዋል።
ክሬምሊን በበኩሉ ፍርድ ቤቱን በዶንባስ በንጹሃን ዜጎች ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎችን ችላ ብሏል ሲል ይከሳል።
እርምጃው ፍርድ ቤቱ እ.ኤ.አ በ2023 በቭላድሚር ፑቲን እና በሩሲያ የህፃናት መብቶች ኮሚሽነር ላይ ከግጭት ቀጣናዎች ህፃናትን ወስደዋል በሚል የእስር ትዕዛዝ ማውጣቱን ተከትሎ የመጣ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X