የትራምፕ የሰላም እቅድ በጋዛ ተጨባጭ ለውጥ አለማምጣቱን ባለሙያዎች ገለጹ

የትራምፕ የሰላም እቅድ በጋዛ ተጨባጭ ለውጥ አለማምጣቱን ባለሙያዎች ገለጹ
በጦርነቱ ሦስተኛ ዓመት መታሰቢያ ፍልስጤማዊው የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር አይማን አል-ራቅብ ለስፑትኒክ እንደተናገሩት፤ ሰርጡ አሁንም ግልጽ የሆነ የመረጋጋት ራዕይ ሳይኖረው ወደማይታወቅ አቅጣጫ ማምራቱን ቀጥሏል።
በነሐሴ ወር መጀመሪያ ላይ በተፋላሚ ኃይሎች ዘንድ ተቀባይነትን ያገኘው የተመድ መልዕክተኛ እቅድ፤ የእስራኤልን ግልጽ ምላሽ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል። አል-ራቅብ ለዚህ መጓተት ምክንያቱ እስራኤል የምርጫ ውጤት እየተጠባበቀች መሆኑ ነው ብለዋል።
እስካሁን የተለቀቁት እስራኤላውያን እስረኞች እንጂ ሁሉም ፍልስጤማውያን እስረኞች አለመሆናቸውን በመጠቆም፤ ተጨባጭ ለውጥ ሊመጣ የሚችለው ከእስራኤል ምርጫ በኋላ ብቻ እንደሆነ ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
የዓረብ ፍልስጤም ጥናትና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር ታየር አቡ አታይዊ በበኩላቸው፤ ወታደራዊ ውጥረት፣ ግድያ፣ የቦምብ ድብደባ እና ውድመት አሁንም የሰርጡን ወቅታዊ የሚገልፁ ናቸው ብለዋል።
ለሰላም ሂደቱ መጓተት እስራኤል የትራምፕን የሰላም እቅድ እና የሻርም ኤል-ሼክን የተኩስ አቁም ስምምነት አለማክበሯን ተጠያቂ በማድረግ፤ በጉዳዩ ዙሪያ የአሜሪካ ግፊት በቂ አለመሆኑንም አመልክተዋል።
ትራምፕ እስራኤል እቅዳቸውን እንድትተገብር እስካላስገደዱ ድረስ የጋዛ እጣ ፈንታ በእንጥልጥል እንደሚቀጥል አቡ አታይዊ ተከራክረዋል። አክለውም ጦርነቱን ለማስቆም የተባበረ ዓለም አቀፍ ጫና እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X