- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል። አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ይህ ፕሮግራምም ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

ትርጉም እና አፍሪካ፡ በቋንቋዎች መካከል ድልድይ መዘርጋት

ትርጉም እና አፍሪካ፡ በቋንቋዎች መካከል ድልድይ መዘርጋት
ሰብስክራይብ
አፍሪካ በሺዎች የሚቆጠሩ ቋንቋዎች መገኛ ስትሆን፤ ይህ የቋንቋ ብዝሃነት ለቀጣናዊ ውህደት እንደ ሀብት ሆኖ ያገለግላል።
"ጥሩ ትርጉም ቃላትን ብቻ ሳይሆን ትርጉምን፣ እሴቶችን፣ ታሪክንና ባህልን ያስተላልፋል። ለአፍሪካ ትርጉም የብዙሃን ቋንቋ ተናጋሪነት ምሰሶ ነው፤ የባህልና የቋንቋ ልዩነቶች እንዳይጋጩ በማድረግ ማህበረሰቦች ሀገር በቀል ቋንቋቸውን እያዳበሩ በሰፊው የውይይት መድረክ ላይ እንዲሳተፉ ያስችላል" ሲሉ አስቻለው ለገሰ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን፣ የሙያዊ የትርጉም አገልግሎት የአፍሪካን ውህደት፣ ትምህርት፣ የሚዲያ ነፃነት እና የደቡብ ለ ደቡብ ትብብር ማጠናከር የሚችልባቸውን መንገዶች እንቃኛለን። በዚህ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡን በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የውጭ ቋንቋዎችና ስነ-ጽሑፍ መምህር እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስና ሁማኒቲስ ኮሌጅ ዲን ከሆኑት አስቻለው ለገሰ (ዶ/ር) ጋር ቆይታ አድርገናል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Deezer – Afripods – Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0