የሱዳኑ አል-ቡርሃን ከአማፂው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል ጋር የሚደረግን ድርድር ውድቅ በማድረግ ሙሉ በሙሉ እስኪሸነፉ ድረስ ለመዋጋት ቃል ገቡ

ሰብስክራይብ

የሱዳኑ አል-ቡርሃን ከአማፂው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል ጋር የሚደረግን ድርድር ውድቅ በማድረግ ሙሉ በሙሉ እስኪሸነፉ ድረስ ለመዋጋት ቃል ገቡ

"ከማንም ጋር ድርድር የለንም፤ ከማንም ጋር እየተነጋገርን አይደለም፤ ከማንም ጋር ምንም የሚያገናኘን ነገር የለም" ሲሉ የሱዳን ጦር አዛዥ አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን በሰሜናዊቷ አምሪ ከተማ ለተሰበሰበው ሕዝብ ተናግረዋል።

የሱዳን ሠራዊት በዳርፉር፣ ኮርዶፋን እና በብሉ ናይል ቀጣናዎች የሚገኘውን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል ድል እስኪያደርግ ድረስ ውጊያውን እንደሚቀጥል የገለጹት አል-ቡርሃን፤ የጦርነት እና የሰላም ውሳኔ የመንግሥት ተቋማት እንጂ የግለሰብ መሪዎች አለመሆኑን አስምረውበታል።

የሱዳን ሠራዊት የቅርብ ግዜ ወታደራዊ ስኬቶች፦

🟠 ሰሜን ኮርዶፋን፦ ሠራዊቱ አል-ማዝሩብ፣ ሶዳሪ፣ እም ሻሮ እና ቢያንስ 11 ሌሎች አካባቢዎችን መልሶ በመቆጣጠር የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን የስንቅ እና የሎጂስቲክስ መስመሮች ዘግቷል።

🟠 ምዕራብ ኮርዶፋን፦ የሱዳን ሠራዊት የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ወታደራዊ አቅሙን አጠናክሮ በተሰባሰበበት እን ናሁድ እና አል ኹዋይ ገስግሷል።

🟠 ደቡብ ኮርዶፋን፦ ሠራዊቱ ከፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ እና ከአጋር ታጣቂዎቹ ጋር ባደረገው ውጊያ በኤል-ኦቤይድ–ዲሊንግ አውራ ጎዳና ላይ የሚገኙ ስትራቴጂካዊ ቦታዎችን ተቆጣጥሯል።

ካርቱም በውጭ ሀገራት የሚደገፈውን አማፂ ሕጋዊ ለማድረግ ያለሙ ናቸው ያለቻቸውን የሰላም ጥረቶች ውድቅ አድርጋለች። በቅርቡ አሜሪካ መሪነት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የአየር  በረራ እገዳ ለመጣል የተደረገው እና ሩሲያ የተቃወመችው ጥረት በዚህ ተጠቃሽ ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0