- Sputnik አፍሪካ, 1920
The African Heights show
ወቅታዊ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች፣ አዳዲስ መረጃዎች እና በደቡባዊው ዓለም ሀገራት መካከል ጠንካራ ትስስር የሚፈጥሩ አበይት ክስተቶች የሚዳሰሱበት ፕሮግራም።

አፍሪካዊያን ወጣቶችን የማብቃት ጉዞ — የነገ መሪዎችን መገንባት!

አፍሪካዊያን ወጣቶችን የማብቃት ጉዞ — የነገ መሪዎችን መገንባት!
ሰብስክራይብ

ተሰጥኦ ዕድልን ይከተላል፤ ዕድሎችም ተቋማት ውጤታማ፣ ተገማች እና ከሁሉም በላይ አካታች በሆኑበት ቦታ ይበለጽጋሉ። አመራር የሚገለጸው በማዕረግ ወይም በሕዝብ ሹመት አይደለም። ይልቁንም በባህሪ፣ በታማኝነት፣ በአገልግሎት እና አዎንታዊ ለውጥን በማነሳሳት ይገለጻል። ትርጉም ያለው ተሳትፎ የሚጀምረው ወጣቶችን በልማት ውስጥ እንደ ተጠቃሚዎች ብቻ ሳይሆን እንደ አጋሮች በመቀበል ነው — አፍሪካ የወጣቶች ችግር የላትም፤ ያላት የዕድል ክፍተት ነው፤ ይህንን ክፍተት መዝጋትም ለእያንዳንዱ የአፍሪካ መሪ ቀዳሚ ተግባር መሆን አለበት። የአፍሪካ ወጣቶች ሊመሩት የሚገባ ችግር ሳይሆኑ፣ ኢንቨስት ሊደረግባቸው የሚገባ ዕድል ናቸው - ሲሉ ከናይሮቢ ኬንያ፣ የአመራር ባለሙያው ጄሚ ማክአፖሎ ለአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራም ተናግረዋል።

ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት የዛሬው የአፍሪካን ሀይትስ ዝግጅት፡-

በክፍል አንድ ሕይወትን እንደገና መገንባት — የሴት ልጆች ግርዛት በአፍሪካ የሚያስከትለው የሕክምናና የሰብዓዊ ዋጋን እንወያያለን። ዶ/ር ቡለንት ቺሃንቲሙር፣ ዝነኛው የፕላስቲክ እና የመልሶ ህክምና ቀዶ ሐኪም ደግሞ ሙያው ትንታኔ ያጋሩናል።

በክፍል ሁለት የአፍሪካ ወጣቶችን ማብቃት — የነገ መሪዎችን ስለመገንባት ዳሰሳ ስናደርግ ከናይሮቢ ኬንያ፣ የአመራር ባለሙያው ጄሚ ማክአፖሎ ሀሳባቸውን ያካፍሉናል።

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0