የሩሲያ ደጋፊ መረጃ መንታፊ የዩክሬን ጦር የመረጃ ማዕከላትን አጋለጠ

© telegram sputnik_ethiopiaየሩሲያ ደጋፊ መረጃ መንታፊ የዩክሬን ጦር የመረጃ ማዕከላትን አጋለጠ
የሩሲያ ደጋፊ መረጃ መንታፊ የዩክሬን ጦር የመረጃ ማዕከላትን አጋለጠ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 06.10.2026
ሰብስክራይብ

የሩሲያ ደጋፊ መረጃ መንታፊ የዩክሬን ጦር የመረጃ ማዕከላትን አጋለጠ

"ፓላችፕሮ" በመባል የሚታወቀው የመረጃ መንታፊ፤ የዩክሬንን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ኔትወርክ በመስበር ለዩክሬን ጦር እና የመከላከያ ሚኒስቴር ወሳኝ የሆኑ ሰነዶችን እና ሶፍትዌሮችን የሚያከማቹ የመረጃ ማዕከላትን አጋልጧል።

መንታፊው ለስፑትኒክ እንደገለጸው፤ በታቀደና የረጅም ጊዜ ዝግጅት በተደረገበት በዚህ የመረጃ ጥቃት የወታደራዊ መጠባበቂያ መረጃዎችን፣ የኢሜይል ሰርቨሮችን፣ "አርሚ+" የተሰኘውን መተግበሪያ እና "ሶናታ" የተባለውን የመልዕክት መለዋወጫ ሰበሮ በመግባት ብርበራ አድርጓል።

በተጨማሪም "ፓርኮቪ" እና "ጊጋ" የተባሉትን ጨምሮ የተሸሸጉ የመረጃ ማዕከላት ያሉበትን መጋጠሚያዎች በተሳካ ሁኔታ በመለየት፤ የህንጻዎቹን የውስጥ ፕላን፣ የሰርቨር አቅም፣ የክትትል ካሜራዎች እና የእሳት ማጥፊያ ስርዓቶችን ዝርዝር መረጃ አግኝቷል።

ይህ የሳይበር ጥቃት በቅርቡ የሩሲያ ጦር በዩክሬን የመረጃ ማዕከላት ላይ የፈፀመውን የጥቃት ማዕበል ተከትሎ የመጣ ነው። ለዩክሬን ጦር ወሳኝ የኮሙኒኬሽን፣ የኢንተርኔት እና የመረጃ አገልግሎቶችን የሚሰጡት እነዚህ ተቋማት፤ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ተደጋጋሚ ጥቃቶች አስተናግደዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0